“አንበሳው ተርቧል” – ዝላታን ኢብራሂሞቪች

ወደ  ኤም ኤል ኤስ ጋላክሲ ያቀናው ዝላታን ኢብራሂሞቪች ትናንት አሜሪካ ሲደርስ የጀግና አቀባበል የተደረገለት ሲሆን “አንበሳው ተርቧል” በማለት ለአዲስ ድል መዘጋጀቱን አሳውቋል።

ተጨዋቹ ጫማውን ከመስቀሉ በፊት በአሜሪካ ቆይታ ለማድረግ ዩናይትድን ተሰናብቶ አቅንቷል።

36 ኛ አመቱ ላይ የሚገኘው ዝላታን በድጋሚ ለጆሴ ሞሪንሆው ቡድን ፊርማውን ቢያኖርም የጉልበት ጉዳቱ አገርሽቶ ክለቡን መጥቀም ሳይችል ተለያይቷል።

ትናንት አሜሪካም ሲደርስ የጀግና አቀባበል የተደረገለት ሲሆን ስሜቱም እንደ ወጣት እንዲሰማው እና ለድል የተራበ እንዳደረገው ተናግሯል።

ዝላታን ዴቪድ ቤካም፣ጄራርድ አሽሊ ኮል እና ሮቢ ኪን በአሜሪካ መጫወታቸው እሱም ወደ እዛው ለማቅናት ምክንያት እንደሆነው ጨምሮ አሳውቋል።

“ወደ ክለባች  እንድገባ ደወሉልኝ እኔም መልስ ሰጠኋቸው።እነሱ በአሜሪካ በጣም ውጤታማው ቡድን ናቸው፣ለእኔም እዚህ ትክክለኛው ቦታ እንደሆነ አስባለው።” ሲል ስሜቱን ገልጿል።

ዝላታን ቀደም ብሎ ወደ አሜሪካ እንደሚያቀና ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ቆይታውን በእንግሊዝ ካደረገ በኋላ መጨረሻውን አሜሪካ አድርጓል።

ተጫዋቹም እራሱ ወደ ዩናይትድ ከማቅናቱ በፊት ወደ አሜሪካ መሄድ ይፈልግ እንደነበር ግልፅ አድርጓል።ከአንድ ወይም ሁለት አመታት በኋላም ጫማውን እንደሚሰቅል ይጠበቃል። 

Advertisements