አለን ፓርዲው ከዌስትብሮም አሰልጣኝነታቸው ተሰናበቱ

አለን ፓርዲው ከዌስት ብሮምዊች አልቢዮን አሰልጠኘታቸው በስምነት መልቀቃቸውን የፕሪሚየር ሊጉ ክለብ ገልፅዋል።

ክለቡ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጠው መግለጫ “በዌስት ብሮምዊች አልቢዮን እና አለን ፓርዲው መካከል የተደረገውን ውይይት ተከትሎ ሁለቱ አካላት ለመለያየት ያጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

“ረዳት ዋና አሰልጣኙ ጆን ካርቨርም ክለቡን የሚለቁ ይሆናል።

“ክለቡ አለን እና ጆንን ላደረጉት ጥረት ማመስገን ይወዳል፤ እንዲሁም ለመጪው ጊዜያቸው መልካም እንዲገጥማቸው ይመኛል።

“ተጨማሪ መግለጫ እስኪወጣ ድረስም የመጀመሪያው ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት ዳረን ሙር ቡድኑን በኃላፊነት የሚረከቡ ይሆናል።

“ክለቡ በዚህ ሰዓት ሌላ ተጨማሪ አስተያየት የማይሰጥም ይሆናል።” ሲል ገልፃዋል።

የ56 ዓመቱ እሰልጣኝ ከዚህ የውድድር ዘመን መጀመሪያ አንስቶ ክለቡን በአሰልጣነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ፓርዲው ከ2011 አንስቶ ክለቡን በአሰልጣኝነት የመሩ ስድስተኛ አሰልጣኝ ሲሆኑ በ18 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማግኘት ከሚገባቸው 54 ነጥቦች መሰብሰብ የቻሉት ስምንት ነጥቦችን ብቻ ነው።

የአለን ፓርዲው ይህ ስንብት የተሰማው ክለቡ ዋና ኃላፊውን ጆን ዊልያምን እና ዋና ስራ አስፈፃሚውን ማርቲን ጉድማንን ካሰናበተ የስድስት ወራት ልዩነት በኋላ ነው።

ዌስት ብሮም ለተከታታይ ስምንት የውድድር ዘመናት በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ተሳትፎ የነበረው ቢሆንም በዚህ የውድድር ዘመን ካደረጋቸው 32 ጨዋታዎች ማግኘት የቻለው 20 ነጥቦችን ብቻ ነው።