“የሊቨርፑል ሶስቱን የፊት መስመር ተጫዋቾችን ለማቆም ከባድ ናቸው”  – ፔፕ ጋርዲዬላ

Related image

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ በመንሀጁል ሀያቲ

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዬላ የሊቨርፑል የአጥቂ መስመር ተጫዋቾችን ማቆም አስቸጋሪ ነው በማለት ለጋዜጠኞች አስተያየቱን ሰጥቷል።

በያዝነው የውድድር አመት አንፊልድ ላይ 4 ጎሎችን በማስቆጠር የማንችስተር ሲቲን በፕሪሚየር ሊጉ ያለመሸነፍ ጉዞ 4 ለ 3 በሆነ ውጤት በማስቆጠር መግታት የቻሉት ሊቨርፑሎች ብቻ እንደሆኑ የሚታወስ ሲሆን፤ ሁለቱ ክለቦች በቻምፒዬንስ ሊጉ እሮብ ምሽት የሚገናኙ ይሆናል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዬላ በሰጠውም አስተያየት : ” ሙሀመድ ሳላህ ብቻ አይደልም, ማኔ እና ፊርሚኖ ሶስቱም ለማቆም ከባድ የሆኑ ተጨዋቾች ናቸው ፤ አስገራሚ ተጫዋቾች ናቸው።”

“የአንፊልዱ ጨዋታ ላይ ምንም መቆጣጠር አልቻልንም ነበር፤ ሊቨርፑሎቹ የሚጫወቱበት መንገድ ለእኛ አስቸጋሪ ነበር ፤ እናውቃለን በጣም ፈጣን እና ጥሩ ናቸው ነገር ግን ይህ ጨዋታ የቻምፒዬንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ነው እንደ ባለፈው አይነት ጨዋታ አይጠበቅም፤ ቀለል ያለ የሚሆን ነገር ይጠበቃል።

” ፔፕ ጋርዲዬላ አንፊልድ ላይ በነበረው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ፊርሚኖ, ሰይዶ ማኔ እና ሙሀመድ ሳላህ በ9 ደቂቃ ውስጥ ሶስት ጎሎችን በማንችስተር ሲቲ ላይ ማስቆጠር እንደቻሉ የሚታወስ ሲሆን፤ እሮብ ምሽት በቻምፒዬንስ ሊጉ የሩብ ፍፃሜ የሚገናኙ ይሆናል።

 

Advertisements