የቡንደስሊጋው 50+1 ህግ ለጀርመን እግርኳስ ትሩፋት ወይስ ጉዳት?

የፕ ሄይንክስ ከ2012-13 የውድድር ዘመን አንስቶ ያለማቋረጥ የቡንደስሊጋውን ዋንጫ ለስድስተኛ ጊዜ እንዲያነሳ ዳግም ወደባየር ሙኒክ ተመልሰዋል።

በዚያ የውድድር ዘመን ባየር ሙኒክ የዋንጫው አሸናፊ ለመሆን ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ ጋር እስከመጨረሻ ድረስ ታላቅ ፍልሚያ አድርጓል። የየርገን ክሎፑን ጠንካራ ቡድንም በሻምፒዮንስ ሊጉ ፍፃሜ ለማሸነፍ የቻለው በእልህ አስጨራሽ ትግል በጭማሪ ሰዓት ግብ 2ለ1 በማሸነፍ ነበር።

በዚህ የውድድር ዘመን ግን ባለፈው ቅዳሜ ታላቅ ተግዳሮት ይሆንበት በነበረው ዶርትሙንድ ላይ በቀላሉ ግማሽ ደርዘን ግብ በማዝነብ ገና ከወዲሁ የቡንደስሊጋው ሻምፒዮን ለመሆን በእጅጉ ከጫፍ ደርሷል። ይህ ደግሞ ቡንደስሊጋው በአውሮፓ ያለውን የጠንካራ ሊግነት ግርማሞገስ በእጅጉ የሚያኮስስ ነው።

ዝቅተኛ የስታዲየም ትኬት ክፍያ፣ ከፍተኛ የተመልካች ቁጥር፣ ጠንካራ ፉክክር፣ ፋና ወጊ የታዳጊዎች ስልጠና፣ እና አብይ የክለቦች የማህበራት አብላጫ የባለቤትነት ድርሻ (ቀጥለን በሰፊው የምንዳስሰው የ50+1 ህግ) እነዚህ ሁሉ የቡንደስሊጋው የአውሮፓ መድረክ የጥንካሬ ምንጭ ነበሩ።

ባየር ሙኒክ ላለፉት አምስት ዓመታት ዶርትሙንድን በአሊያንዝ አሬና ሲያስተናግድ ከዚህ ቀደም የነበረው የሁለቱ ክለቦች ፉክክር አሁን ደብዝዟል። ቡንደስሊጋውም ወደአንድ ቡድን የበላይናት ያመዘነ ሆኗል፤ ወደባቫሪያኑ።

ሆኖም አሁን ላይ ውጤታማነቱ በእጅጉ አጠራጠሪ ቢሆንም ይህን ልዩነት እንዲያስቀር ታስቦ እ.ኤ.አ. 1998 የ50+1 ህግ በቡንደስሊጋው ላይ ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል።

50+1 ምንድን ነው?

ክለቦች በጀርመኑን የእግርኳስ ሊግ ተሳታፊናት ፈቀድን ለማግኘት በክለባቸው የሃብት ድርሻቸው ላይ አብላጫ መብት ሊኖራቸው እንዲገባ የሚያስገድድ ህግ ነው። ህጉ እንዲወጣ ምክኒያት የሆነው ደግሞ ክለቦችን ከውጪያዊ ባለሃብቶች ተፅእኖ በማላቀቅ የክለቡ የሃብት ድርሻ በክለቡ አባላት አጠቃላይ ቁጥጥር ስር እንዲሆን ታስቦ ነው።

የህጉ መሰረት

ከ1998 በፊት የጀርመን እግርኳስ ክለቦች በራሳቸው በክለቡ አባል ማህበራት የባለቤትነት ሙሉ ቁጥጥር ስር ይገኙ ነበር። ይህ ማለት ደግሞ ክለቦች ይንቀሳቀሱ የነበረው ለትርፍ እንደሚንቀሳቀሱ ተቋማት አልነበረም። በማንኛውም ሁኔታም የግል ባለቤትነት የሚፈቀድ ነገር አልነበረም። በዚህ ምክኒያት የጀርመን እግርኳስ ማህበር ይህን ህግ በ1998 እንዲያወጣ አድርጓል። በመሆኑም ክለቦች የእግርኳስ ቡድኖቻቸውን ወደህዝብ ወይም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ደረጃ እንዲቀይሩ አስችሏቸዋል። ይሁን እንጂ የ”50+1″ ህግ አንድ የክለብ ኩባንያ አብላጫ የድምፅ መብት እንዲኖራቸው ለማረጋገጥ ሲል አባላቱ ከባለቤትነት ድርሻው ቢያንስ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ መያዝ እንደሚኖርባቸው ያስገድዳል። ሆኖም አንድ ግለሰብ ወይም ኩባንያ አንድን ክለብ ያለማቋረጥ ለ20 ዓመታት በገንዘብ የሚደግፍ ከሆነ ግለሰቡ ወይም ኩባንያው የክለቡን የሃብት ድርሻ በባለቤትነት የመቆጣጠር መብት ይኖረዋል። ይህ መብትም በባየር ሌቨርኩሰን (ባየር በተሰኘው የህክምና መድሃኒትና መሳሪያዎች ፋብሪካ) እንዲሁም በዎልፍስበርግ (በተሽከርካሪ አምራቹ ሾልስዋገን) ላይ ተግባራዊ ሆኗል።

የህጉ ክፍተቶች

ህጉ በተለያዩ ጊዜያት ተቃውሞዎች ሲነሱበት ቆይቷል። ከህጉ ቀንደኛ ተቃዋሚ ክለቦች መካከል አንደኛው ሃኖቨር 96 ክለብ ነው። የዚህ ክለብ ፕሬዝዳንት የሆኑት ማርቲን ካይንድ የአውሮፓ ህብረትን የውድድር ህግ እንደሚፃረር በማንሳት በህጉ ላይ ያላቸውን የሰላ ተቋውሞ ከሚያቅርቡ ግለሰቦች መካከል ይጠቀሳሉ። በመሆኑም በ2009 ሃኖቨር ህጉ እንዳቀየር ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ነገር ግን የተቃውሞ ጥያቄው ከ36ቱ አባል ክለቦች በ32ቱ ውድቅ እንዲሆን ተደርጓል።

ይሁን እንጂ አርቢ ሌፕዢግ ህጉ በሚገባ ተግባራዊ እየተደረገ ላለመሆኑ ለማሳያነት የሚቀርብ ክለብ ነው። ምንም እንኳ በአርቢ ሌፕዢግ አባላጫ ተሰሚነት ያላቸው የክለቡ አባል ባለቤቶች በንድፈሃሳብ ደረጃ ቢኖሩም ነገር ግን ምንም አይነት ምክኒያት ማቅረብ ሳይገባቸው የየትኛውንም የቡድን አባላት ጥያቄ ውድቅ የማድረግ መብት ያላቸው ተጠባባቂ አባላት ያሉት ክለብ ነው። ከእነዚህ አባላት ደግሞ አብዛኞቹ የኃይል መጠጥ አምራቹ ሬድ ቡል ኩባንያ ሰራተኞች ናቸው። በዚህ ላይ የክለቡ ዓመታዊ የአባልነት ክፍያ ከሌሎቹ ክለቦች ጋር ሲነፃፀር ውድ የሚባል ነው።

ባለፈው ሳምንት ሳምንት የቡንደስሊጋ እና የቡንደስሊጋ 2 ክለቦች ህጉ እንዲቀጥል ድምፃቸውን ቢሰጡም ነገረ ግን ህጉ ከከዚህ ቀድሙ በላቀ የጎሉ የተቃውሞ ድምፃች ተሰምተውበታል።

ዝቅተኛ የስታዲየም መግቢያ ትኬት ዋጋ እና በተመልካች የተሞሉ ስታዲየሞች መኖራቸው በጀርመን የእግርኳስ አፍቃሪው ህዝብ ዘንድ የ50+1 ህግ እንደኩራት ምንጭ ሊወሰድ ይችላል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይም ይህን በጉልህ የሚየሳዩ ከ”#50+1 ጋር እንቆይ” የሚሉ ቅስቀሳዎች በስፋት ታይተዋል።

ይህ ግን የአስተዳደራዊ ሂደቱን እውነታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አይመስልም። አርቢ ሌፕዢግ ከዝቅተኛው ዲቪዚዮን ፈጣን የሆነ ማንሰራራት በማሳየት እስከሻምፒዮምስ ሊግ ውድድር መብቃት የመቻሉ ሚስጥር በበግዙፉ የኃይል መጠጥ አምራቹ ሬድ ቡል መታገዙ ነው። ኩባንያው የ50+1 ህግን ሳይጥስ ተግብራዊ ቢያደርግም ከላይ እንደተጠቀሰው የአባልነት ክፍያ ዋጋን ከፍ በማድረግ እና አብዛኞቹን የኩባንያውን ሰራተኞች በአባልነት በማሳተፍ በክለቡ የባለቤትነት ድርሻ ላይ ረጅም እጅ አለው።

እንዲሁም ከባየር ሌቨርኩሰ እና ዎልፍስበርግ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ በንድ ኩባንያ የባለቤትነት ድርሻ መጠቃለል በተጨማሪ በቅርቡ የሳፕ የሶፍትዌር ቢሊየነሩ ዲትማር ሆፕ ሆፈኒየምን በብቸኛ የበለሃብትነት የመምራት መብትን ማግኘት ችሏል።

የሃኖቨሩ የክለብ ኃለፊ የሆኑት ማርቲን ካይንድም ህጉ በሚሰጠው የ20 ዓመታት ገደብ መሰረት ክለቡን በተመሳሳይ መንገድ ለመጠቅለል ዕቅድ ያለቸው ሰው ናቸው።

ባየር ሙኑክ በግንቦት ወር የድል ሻምፓኙን ለመክፈት ሲዘጋጅ የ50+1 ህጉ ምንም የተለየ ተዓምራዊ ቀመር እንደሌለው በግልፅ የሚየሳይ ይሆናል።

“የጀርመን እግርኳስ ሊግ የ50+1 ህግን ወደዚያ አሽቀንጥሮ እንደሚጥለው ተስፋ አለኝ።” ሲሉ የባይር ሙኒክ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ከርል-ሄንዝ ሩምኔዥ በቅርቡ ከጂኪው ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ተናግረው “ትንሽ ከፍ ያለ ፉክክር ቢኖር አወዳለሁ።” ብለዋል።

ሩምኔዥ ይህን ይበሉ እንጂ ክለባቸው ማንኛውንም ዕድል ሲያገኝ ከቀንደኛ ተፎካካሪያቸው ሻልከ ድንቁን ተከላካይ ሊዮን ጎሬዝካን በማንኛውም ዕድል በቀላሉ ለማስፈረም መቻላቸው ለዚህ የስፖርት ተፎካካሪነት የመጥፋቱ ጉዳይ የቅርብ ምሳሌ ነበር።

በወቅታዊው ህግ መሰረት ባየር ሙኒክ ኦዲ፣ አዲዳስ እና አሊያንዝ የተሰኙት ኩባንያዎች በባለቤትነት ድርሻው ላይ ቁልፍ የቢዝነስ አጋሮቹ ናቸው። በመጪው ኃምሌ ወር ደግሞ የኳታር አየር መንገድ ተጨማሪ ይፋዊ አጋራቸው ይሆናል።

ሰንሰለቱ ከቡንደስሊጋው ሲላቀቅ ያን ጊዜ አዲሱ ገንዘብ ወዴት ፈሰስ እንደሚሆን ግልፅ ይሆናል።

የውጪያዊ የባለቤትነት ገደብን አንድ ክለብ ምን ያህል ማጥበብ እንደሚችል የሌፕዚግ ጉዳይ በጉልህ የሚያሳይ ነው። በዚህ አተያይ ደግሞ ባየር ሙኒክ ምን ያህል በቡንደስሊጋው ላይ ያለውን የበላይነት አጠንክሮ ማስቀጠል እንደሚችል ማሰብ ይቻላል።

የሊጉ የመረጋጋት ጉዳይ

ባየር ሙኒክ እንደእንድ የጀርመን ብቸኛ ልዕለ ኃያል ክለብ የ50+1 ህግ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊትም ሆነ በኋላ የተደላደሉ መዋቅራዊ ዕድሎች ያሉት ክለብ ነበር። የዚህ ኃያልነቱ ምክኒያት ደግሞ አስደናቂ የድጋፍ መሰረት እና በእጅጉ ከፍ ያለ እና የበላይነቱን የሚያስመሰክር የተረጋጋ የገንዘብ አቅም ያለው መሆኑ ነው።

ባቫሪያኑ አሁንም በላይነታቸው ይቀጥላሉ። ከስድስት ወራት በፊት ካርሎ አንቸሎቲን እንዳደረጉት ሁሉ ሲያሻቸው የርገን ክሊንስማንን ወይም ዎብልን በአሰልጠኝነት ሊቀጥሩ ይችላሉ። ዶርትሙንድ ደግሞ ድንቅ የነበረውን አሰልጣኝ አሰናብቶ ከክለቡ ጋር ጥልቅ የሆነ አቅም የሌላቸውን ፒተር ቦዥሽ ለመቅጠር መገደዱን ሊቀጥል ይችላል።

ባየር በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት 28ኛ የቡንደስሊጋ ዋንጫውን ሲያነሳ፣ ዶርትሙንድ ግን ያነሳው ዋንጫ አሁንም ስምንት ብቻ እንደሆነ ባታሪክ ላይ ተመዝግቦ ይቀጥላል። ይህ የፉክክር መንፈስ ነው እንግዲህ ዶርትሙንድም ሆኖ ሌሎች ክለቦች እንደባለራዕዩ የርገን ክሎፕ አይናት አዲስ ነገር ፈጣሪ አስልጣኝ እንዲኖራቸው ተስፋ እያደረጉ መጪውን ጊዜ የሚቀጥሉበት።

Advertisements