“ሀሙስ ተመልሰው ይመጣሉ” – አርሴን ቬንገር

Image result for arsene wenger

አርሴን ቬንገር አርሴናል ስቶክ ሲቲን 3 ለ 0 ባሸነፉበት ጨዋታ ላይ ብዙ ወንበሮች ያለ ተመልካች ባዶ መሆናቸውን ተከትሎ ደጋፊዋቹ ለአውሮፖ ሊጉ ጨዋታ ተመልሰው ወደ ሜዳ ይመጣሉ ሲሉ ተደምጠዋል።

አርሴናል በሜዳው ኤምሬትስ ስታዲዬም ስቶክ ሲቲን ሲያሸንፍ ሜዳ ውስጥ ደጋፊ የናፈቃቸው ብዙ ወንበሮች ባዶ መሆናቸውን ተከትሎ አርሴን ቬንገር ለጋዜጠኞች በሰጡት ሀሳብ

፦ ” ይህ የማይካድ እውነታ ነው እኛ በአሁኑ ስአት ለሻምፒዬንነት አይደለም እየተጫወትን ያለነው፤ ይህንንም መቀየር እንደማንችል ደጋፊዋቹ ያውቃሉ፤ ነገር ግን አታስቡ ሀሙስ ተመልሰው ይመጣሉ።”

ርሴን ቬንገር አርሴናል በፕሪሚየር ሊጉ አሁንም ከአራቱ በ13 ነጥቦች እርቆ ስድስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ሀሙስ በሜዳው ኤምሬትስ ስታዲዬም በአውሮፖ ሊጉ ጨዋታ ኬስካ ሞስኮን የሚያስተናግድ ይሆናል።

Advertisements