በሳለህ የተያዙና ገና ሊያዙ የሚችሉ ክብረወሰኖች

መሐመድ ሳላህ ቅዳሜ ሊቨርፑል ክሪስታል ፓለስን 2ለ1 ማሸነፍ በቻለበት ጨዋታ ላይ በውድድር ዘመኑ በፕሚየር ሊጉ ያስቆጠራቸውን ግቦች 29 በማድረስ ክብረወሰኖችን የመሰባበር ጉዞውን ቀጥሎበታል።

ተከታዩ ፅሁፍም ሳለህ እስካሁን የያዛቸውን እና የሰበራቸውን ክብረወሰኖች እንዲሁም ሁለት ወራት በቀሩት የውድድር ዘመን ገና ሊሰብራቸው ስለሚችላቸው ክብረወሰኖች የኦፕታን ቁጥራዊ መረጃ መሰረት አድርጎ በዝርዝር ይተነትናል።

ሳላህ የወርቅ ጫማ ፉክክሩን ከሃሪ ኬን በአምስት ግቦች በልጦ እየመራ ይገኛል

የሰበራቸው ክብረወሰኖች

በፕሪሚየር ሊጉ በአንድ የውድድር ዘመን ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ የሊቨርፑል ተጫዋች


ሳላህ በእንድ የውድድር ዘመን በአጠቃላይ ያስቆጥራቸው 37 ግቦች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከተጀመረበት ጊዜ ወዲህ በአንድ የሊቨርፑል ተጫዋች የተቆጠረ ከፍተኛ ግብ ነው። በዚህም በ1995/96 የውድድር ዘመን ሮቢ ፎውለር አስቆጥሯቸው የነበሩትን አጠቃላይ 36 ግቦችን በመብለጥም ክብረወሰኑን መስበር ችሏል። ሮቢ ፎውለር በ53 ጨዋታዎች ካስቆጠራቸው 36 ግቦች ጋር ሲነፃፀር ግን በሳላህ የተቆጠሩት በ41 ጨዋታዎች ላይ መሆኑ ክብረወሰኑን አስደናቂ ያደርገዋል።

– በመጀመሪያ የውድድር ዘመኑ ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ የሊቨርፑል ተጫዋች


ሳላህ በመጀመሪያ የውድድር ዘመኑ ፕሪሚየር ሊጉ ከተጀመረበት ጊዜ ወዲህ በ2007/08 በመጀመሪያ የውድድር ዘመኑ 33 አጠቃላይ ግቦችን ማስቆጠር የቻለውን ፈርናንዶ ቶሬስን በልጦ በሊቨርፑል አስደሳች የውድድር ዘመን እያሳለፈ ይገኛል።

ሳላህ ስድስት ጨዋታዎች በቀሩት የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን 29 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል

– በግራ እግሩ ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ


ሳላህ ባለፈው ቅዳሜ በሴልኸረስ ፓርክ ያስቆጠራት 29ኛ የፕሪሚየር ሊግ ግብ አብዝቶ በማይጫወትበት ቀኝ እግሩ የተቆጠረች ናት። ነገር ግን ተጫዋቹ በውድድር ዘመኑ ካስቆጠራቸው አጠቃላይ ግቦች 22ቱ የተቆጠሩት በግራ እግር ነበር። ይህ ደግሞ በአንድ የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን በግራ እግር ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ያሰኘዋል።

– ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ ግብፃዊ ተጫዋች


ሳላህ የግብፅን ባንዲራ በእንግሊዝ በኩራት ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ማድረግ ችሏል። በዋትፎርድ 22 ግቦችን ማስቆጠር ከቻለው ሌላው ግብፃዊ ሚዶ በመብለጥ ከወዲሁ በአብይ የሊግ ውድድሮች ላይ በእንግሊዝ ታሪክ ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ ግብፃዊ ተጫዋች ተሰኝቷል። ይህ ብቻም ሳይሆን በየአንዳንዱ ጨዋታ ላይ ሁለት እና ከዚያ ባላይ ግቦችን ማስጠር የሚችል የመጀመሪያው ግብፃዊ ተጫዋችም ሆኗል።

ሳላህ በሴልኸረስት ፓርክ የማሸነፊየዋን ግብ ከቅርብ ርቀት ማስቆጠር ችሏል

– በፕሪሚየር ሊጉ በአንድ የውድድር ዘመን ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ አፍሪካዊ ተጫዋች


ሳላህ በክሪስታል ፓላስ ላይ ያስቆጠራት ግብ ከበአንድ የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን በአንድ የአፍሪካ ተጫዋች የተቆጠረች ከፍተኛ ግብ በመሆን በ2009/10 የውድድር ዘመን ለቼልሲ 29 ግቦችን ማስቆጠር ከቻለው ዲዲየ ድሮግባ ጋር እንዲስትካከል አድርጋዋለች።

– በአንድ የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን በብዙ ጨዋታዎች ላይ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች


ሳላህ በዚህ የውድድር ዘመን በ21 የተለያዩ ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር በ38 ጨዋታ ይህን ያህል ጨዋታዎች ላይ ተመሳሳይ ግብ ማስቆጠር ከቻሉት ክርስቲያኖ ሮናልዶ (በ2007/8) እና ሮበን ቫን ፐርሲ (2012/13) ጋር በእኩል ደረጃ ተቀምጧል።

በሚደንቅ ሁኔታም ሳላህ በዚህ የውድድር ዘመን መረባቸውን መድፈር ያልቻለበቻው ክለቦች ማንችስተር ዩናይትድና ስዋንሲ ሲቲ ክለቦች ብቻ ናቸው።

ገና ሊስብራቸው የሚችላቸው ክብረወሰኖች

– በአንድ የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች


ሳላህ በአንድ የውድድር ዘመን በ38 የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ከፍተኛ ግብ አስቆጠሪነት ክብረወሰኑን ለመጨበጥ ሁለት ግቦችን ብቻ ማስቆጠር ይበቃዋል። ከዚህ ቀደም ይህን ክብረወሰን መጨበጥ የቻሉት ሶስት ተጫዋቾች ናቸው። (ልዊስ ስዋሬዝ በ2013/14፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2007/08 እና አለን ሼረር በ1995/96 የውድድር ዘመን)ነገር ግን ገና ስድስት ጨዋታዎች የሚቀሩ በመሆናቸው ሳለህ አነዚህን ተጫዋቾች በልጦ ክብረወሰኑን መስበር እንደሚችል ይታሰባል።

– በአንድ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረና የግብ ዕድል ያመቻቸ ተጫዋች


ሳላህ ማስቆጠር ከቻላቸው 29 የፕሪሚየር ሊግ ግቦች በተጨማሪ ለክለቡ ዘጠኝ ግቦች መቆጠር የግብ ዕድሎችን በማመቻቸት የራሱን አስተዋፅኦ ማደርግ ችሏል። ይህ ማለት ደግሞ ቴሪ ሆነሪ በ2002/03 ካስመዘገባቸው ጥምር 24 የግብ ማስቆጠር እና የ20 ግብ ዕድል የማመቻቸት ቁጥር ጋር ላይ ለመድረስ የቀረው ስድስት ግብ ማስቆጠርና የግብ ዕድል የማመቻቸት አስተዋፅኦ ብቻ ነው።

-በአንድ የውድድር ዘመን በከፍተኛ የሊግ ውድድሮች ላይ ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ የሊቨርፑል ተጫዋች


ሳላህ በዚህ የውድድር ዘመን በ38 ጨዋታዎች ላይ 32 ግቦችን የሚያስቆጠር ከሆነ አሁን ክብረወሰኑን ይዞ የሚገኘው ኢያን ራሽ ሊቨርፑል የዋንጫ ባለቤት መሆን በቻለበት 1983/84 የውድድር ዘመን ላይ ማስቆጠር ከቻላቸው 32 ግቦች ጋር የሚስተካከል ይሆናል።

– በአንድ የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች ላይ ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ የሊቨርፑል ተጫዋች


ሳለህ በሁሉም ውድድሮች ላይ ኢያን ራሽ በ1983/84 ያስቆጠራቸው 47 የግብ ክብረወሰን ላይ ለመደረስ 10 ግቦች ያስፈልጉታል። ይህን ማሳከት አስቸጋሪ ቢመስልም ሳላህ ግን ይህ የውድድር ዘመን ከመጠናቀቁ በፊት ሊጫወታቸው የሚችላቸው ቀሪ አምስት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች እና ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች አሉት።

-ከብዙ ቡድኖችን በላይ ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ አንድ ተጫዋች


ሳለህ በፕሪሚየር ሊጉ በዚህ የውድድር ዘመን ያስቆጠራቸው 29 ግቦች ከአራት የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች (ስዋንሲ፣ ኸደርስፋድ፣ በርንሌይና ብራፕተን) ሲልቅ ከሳውዛምፕተን እና ከስቶክ ሲቲ ጋር ደግሞ እኩል ናቸው። ይህ ማለት ደግሞ በእንግሊዝ ከፍተኛ ሊጎች ታሪክ በአንድ የውድድር ዘመን ከሁለት በላይ ከሆኑ ክለቦች የሚልቅ ከፍተኛ ግብ ማስቆጠር የቻለ የመጀመሪያው ተጫዋች ያደርገዋል።

Advertisements