“በጣሊያን የአሰልጣኝነት ጊዜዮ አልቋል”- ማስሚላኖ አሌግሪ

Image result for massimo allegri

 

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ በመንሀጁል ሀያቲ

አሰልጣኝ ማስሚላኖ አሌግሪ ከጁቬንቱስ እንደለቀቁ ከጣሊያን ወጣ ብለው ማሰልጠን እንደሚፈልጉ ተናገሩ።

ስማቸው በተደጋጋሚ ከአርሴናል እንዲሁም ከ ቼልሲ ክለቦች ጋር እየተያያዘ የሚገኘው ጣሊያናዊዬ የጁቬቱስ አሰልጣኝ ማስሚላኖ አሌግሪ ከጣሊያን ወጣ ብለው ማሰልጠን እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

በአሮጊቷ ቤት በተከታታይ ለ4ተኛ ጊዜ የሴሪ ኤውን ዋንጫ ለማንሳት ግስግሴ ላይ የሚገኙት ኤሌግሪ ፤ ከጣሊያን ወጥተው የመስራት እቃዳቸውን ከዘ ቴሌግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ በሰጡት ሀሳብ አሳውቀዋል:: ” እውነቱ ወደ ውጭ ሀገር መሄድ ፈልጋለው፤ በጣሊያን ጨርሻለሁ ”

አሌግሪ አሰልጣኙ ከሴር ኤው በተጨማሪ ባለፈው የውውድር አመት በቻምፒዬንስ ሊጉ ጁቬንቱስን ለፍፃሜ ማድረሳቸው የሚታወስ ሲሆን በሪያል ማድሪድ ተሸንፈው ዋንጫውን ማጣታቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን በያዝነው የውድድር ዘመን በሻምፒዬንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ከማድሪድ ጋር መደልደላቸው የሚታወስ ነው።

Advertisements