ጁቬንቱስ ከ ሪያል ማድሪድ፡ የሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

ጁቬንቱስ በሻምፒዮንስ ሊጉ የሩብ ፍፃሜ የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ጨዋታ ማክሰኞ ምሽት በቱሪን ሪያል ማድሪድን ያስተናግዳል።

ይህ ሁለቱ ክለቦች በ2017 ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ከተገናኙ ወዲህ የሚያደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ሲሆን፣ ባለሜዳው ክለብ በዚነዲን ዚዳኑ ቡድን የደረሰበትን ሽንፈት ቀልብሶ ለመልሱ ጨዋታ ስንቅ የሚሆነውን ውጤት ለመያዝ ተስፋ በማድረግ ይህን ጨዋታ የሚያደርግም ይሆናል።

በሌላ በኩል ማድሪድ ለተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ዕቅድ ይዞ ይህን ከሜዳው ውጪ የሚያደረገውን ጨዋታ ለማሸነፍ አሊያም ግብ አስቆጥሮ ለመመለስ የሚጫወት ይሆናል።

የቡድን ዜናዎች


ጁቬንቱስ

ሚራለም ፒያኒች እና መድሂ ቤናሺያ ሁለቱም በቅጣት ምክኒያት በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፉ ሲሆን፣ ጆርጂዮ ቸሊኒ፣ አሌክስ ሳንድሮ እና ሮድሪጎ ቤንታንኩር ደግሞ ለመልሱ ጨዋታ መሰፍ እንዳይችሉ የሚያደረጋቸው የቢጫ ካርድ አደጋ ያለባቸው ተጫዋቾች ናቸው። ፌዴሪኮ በርናርደሺ እና አሌክስ ሳንድሮ ወደልምምድ የተመልሱ ተጫዋቾች ቢሆኑም፣ ማሪዮ ማንዙኪች ግን በዚህ ጨዋታ ላይ መሰለፉ አጠራጣሪ የሆነ ተጫዋች ነው።

ሪያል ማድሪድ

በሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታ ላይ ረፍት ተሰጥቶት የነበረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዚህ ጨዋታ ላይ ዳግመኛ ቡድኑን ይቀላቀላል። ሪያል ማድሪድ ቅዳሜ ላስ ፓልማስን 3ለ0 በረታበት ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ተቀይሮ የወጣው ናቾ በዚህ ጭዋታ ላይ የመስለፉ ነገር አጠራጣሪ ነው። ኢስኮ ወይም ማርኮ አሰንሲዮ በቱሪኑ ጨዋታ የጋርዝ ቤልን ቦታ ተክተው እንደሚጫወቱም ይጠበቃል። ሰርጂዮ ራሞስ ደግሞ ለመልሱ ጨዋታ ስጋት የሆነ ቢጫ ካርድ ያለበት ብቸኛ የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ነው።

ግምታዊ አሰላለፎች


የጨዋታው እውነታዎች


  • ሪያል ማድሪድ ካደረጋቸው ያለፉት 21 የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች በ20ዎቹ ላይ ከ2.5 በላይ ግቦች ማስቆጠር ችሏል።
  • ሪያል ማድሪድ በሻምፒዮንስ ሊጉ ካደረጋቸው ያለፉት 21 ጨዋታዎች በ17ቱ ላይ ቢያንስ 2 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።
  • ጁቬንቱስ በሁሉም ውድድሮች ላይ ከሪያል ማድሪድ ጋር ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ከ2.5 ግቦች በላይ አስቆጥሯል።
  • ሪያል ማድሪድ ለመጨረሻ ጊዜ ያደረጋቸውን ያለፉት አራት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ችሏል።
  • ጁቬንቱስ በሻምፒዮንስ ሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት 7 ጨዋታዎች ሽንፈት አልደረሰበትም።
  • ጁቬንቱስ በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጋቸው ያለፉት 3 ጨዋታዎች ቢያንስ 2 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።
  • ጁቬንቱስ በሁሉም ውድድሮች ላይ በሜዳው ካደረጋቸው ያለፉት 13 ጨዋታዎች በ11 ጨዋታዎች ላይ መረቡን አላስደፈረም።
  • ሪያል ማድሪድ በሁሉም ውድድሮች ላይ ካደረጋቸው ያለፉት 13 ጨዋታዎች 11 ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችሏል።
  • ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለክለቡና ለሃገሩ ባደረጋቸው ያለፉር 13 ጨዋታዎች 23 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ደብዝዞ የነበረውን ግብ የማስቆጠር ብቃቱን መልሶ ማግኘት ችሏል።
Advertisements