ፍቺ / ጂሚ ፍሎይድ ሀሰልባንክ ከኖርዝሀምፕተን አሰልጣኝነት ተሰናበተ

 

ጂሚ ፍሎይድ ሀሰልባንክ ቡድኑ ኖርዝሀምፕተን በፒተርበርፍ 2-0 መረታቱን ተከትሎ ከወራጅ ቀጠናው ያለው ርቀት ሁለት ብቻ በመሆኑ ከክለቡ አሰልጣኝነት ተሰናብቷል። 

ከ 2017 መስከረም አንስቶ የታችኛውን ሊግ ክለብ በአሰልጣኝነት የተረከበው የቀድሞው የቼልሲ ተጫዋች ባለፉት ዘጠኝ የኖርዝሀምፕተን ጨዋታዎች ላይ ድልን ማሳካት ሳይችል ሲንገታገት ቆይቷል። 

የሀሰልባንክን ከክለቡ መልቀቅ ተከትሎም ምክትሉ ዲን ኦስቲን ለቀሪዎቹ አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ክለቡን በሞግዚትነት እንደሚረከቡ ተገልጿል። 

የ 46 አመቱ ሆላንዳዊ በቼልሲ ከነበረው የአራት አመታት ተፅዕኖ አሳዳሪ የተጫዋችነት ቆይታ በተጨማሪ የሊድስ፣ የአትሌቲኮ ማድሪድ እና መሰል ሌሎች ክለቦችን ማሊያ ማጥለቅ ችሏል።

Advertisements