ሊቨርፑል ከ ማን ሲቲ፡ የሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

ሊቨርፑል በሳምንቱ አጋማሽ በሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ጨዋታ ከአስር ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንችስተር ሲቲን በአንፊልድ ያስተናግዳል።

ቀዮቹ በዚህ የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ ሲቲን በጥር ወር 4ለ3 በሆነ ውጤት ማሸነፍ የቻሉ ብቸኛ ቡድን ቢሆኑም በሜቸው የሚያዳረጉትን ይህ የመጀመሪያ ጨዋታ በጥንቃቄ እንደሚያዳረጉት ግን ይጠበቃል።

ሁለቱም ክለቦች ሩብ ፍፃሜውን የተቀለቀሉት 16 ክለቦች ተሳታፊ በነበሩበት የማጣሪያ ጨዋታቸው በፓርቶ እና ባሰል ላይ በድምሩ 10 ግቦችን በማስቆጠር ነበር። በዚህኛው ዙር ላይ ግን ከባድ የሚባል ጨዋታ ገጥሟቸዋል።

የጨዋታ ጊዜ

ሊቨርፑል ማንችስተር ሲቲን በአንፊልድ ዛሬ (ረቡዕ) ምሽት 3፡45 ላይ ያስተናግዳል።

የጨዋታ ቀጥታ ስርጭት

ይህን ጨዋታ በእንግሊዝ ቢቲ ስፖርት 2፣ ከሰሃራ በታች በአፍሪካ ሱፐር ስፖርት 3 እና በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ ሃገራት ደግሞ ቤን ስፖርት 11 ላይ በቀጥታ መመልከት ይቻላል።

የቡድን ዜናዎች

የሊቨርፑል የተከላካይ ክፍል እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ጉዳት የገጠመውን ዮል ማቲፕን ጨምሮ በጉዳት ታምሷል።

ራግነር ክላቫን እና ጆ ጎሜዝም በጉዳት ምክኒያት የማይሰለፉ የተከላካይ ክፍል ተጫዋቾች ሲሆኑ፣ የክሎፕ ብቸኛው የዋናው ቡድን የመሃል ተከላካዮች ደዣን ሎቭረን እና ቪርጃ ቫን ዳይክ ናቸው።

በቅዳሜ ዕለቱ ጨዋታ የቋንጃ ጉዳት የገጠመው አዳም ላላናም ለበርከታ ሳምንታት ከሜዳ የሚርቅ ሲሆን፣ ሌላው አማካኝ ተጫዋች ኤምሬ ቻና በጀርባው ላይ በገጠመው ጉዳት ምክኒያት በዚህ ጨዋታ ላይ መሰለፉ አጠራጣሪ ነው።

የሊቨርፑል የቡድን ስብስብ፡ ካሪዩስ፣ አሌክሳንደር-አርኖልድ፣ ቫን ዳይክ፣ ሎቭረን፣ ሮበርትሰን፣ ሚልነር፣ ሄንደርሰን፣ ዊይንልደም፣ ሳለህ፣ ፊርሚኖ፣ ማኔ፣ ሚኞሌ፣ ክላይን፣ ማስተርሰን፣ ሞሬኖ፣ ኦክስሌድ-ቻምበርሌን፣ ሶላንኬ፣ ኢንግስ

የማንችስተር ሲቲው ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሰርጂዮ አጉዌሮ ከመጀመሪያው ጨዋታ ውጪ ነው።

በዚህ የውድድር ዘመን 30 ግቦችን ማስቆጠር የቻለው አርጄንቲናዊው ተጫዋች በደረሰበት በጉልበት ጉዳት ላለፉት ሶስት ሰምንታት ወደሜዳ አልገባም።

የመሀል ተከላካዩ ጆን ስቶንስ በጭንቅላቱ ላይ ከደረሰበት ጉዳት አገግሞ ለዚህ ጨዋታ ዝግጁ ሲሆን፣ የግራ ተከላካዩ ፋቢያን ደልፍም ከደረሰበት የግጭት ጉዳት አገግሟል። ሌላኛው የግራ መስመር ተከላካይ ቤንጃሚን ሜንዲ የገጠመው የጉልበት ጉዳት አሁንም ድረስ ወደሜዳ እንዲመለስ አያደርገውም።

የማንችስተር ሲቲ የቡድን ስብስብ፡ ኤደርሰን፣ ብራቮ፣ ዎከር፣ ዳኒሎ፣ ኦታሜንዲ፣ ስቶንስ፣ ኮምፓኒ፣ ላፖርቴ፣ ዚንቼንኮ፣ ዴልፍ፣ ቱሬ፣ ጉንዶጋን፣ ፈርናንዲንሆ፣ ዴ. ሲልቫ፣ ደ ብሩይኔ፣ በ. ሲልቫ፣ ሳኔ፣ ስተርሊንግ፣ ፎደን፣ ዲያዝ፣ ኼሱስ

ግምታዊ አሰላለፎች

ሊቨርፑል የመጀመሪያ ግምታዊ አሰላለፍ፡ ካሪዩስ፣ አሌክሳንደር-አርኖልድ፣ ሎቭረን፣ ቫን ዳይክ፣ ሚልነር፣ ዊናልደም፣ ሄንደርሰን፣ ቻን፣ ሳላህ፣ ፊርሚኖ፣ ማኔ

ማንችስተር ሲቲ፡ ኤደርሰን፣ ዎከር፣ ኦታሜንዲ፣ ኮምፓኒ፣ ዳኒሎ፣ ደ ብሩይኔ፣ ፈርናንዲንሆ፣ ሲልቫ፣ ስተርሊንግ፣ ኼሱስ፣ ሳኔ

Advertisements