ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ተጨማሪ የሻምፒዬንስ ሊግ ታሪክ መስራት ችሏል

 

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ በመንሀጁል ሀያቲ

ፖርቹጋላዊዬ የሎስ ብላንኮዋቹ የፊት መስመር ተጨዋች ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ሪያል ማድሪድ ጁቬንቱስን 3 ለ 0 ባሸነፈበት የቻምፒዬንስ ሊግ ጨዋታ ጎሎችን በማስቆጠር ተጨማሪ የቻምፒዬንስ ሊግ ታሪክ መስራት ችሏል።

ሮናልዶ በጨዋታው ላይ ሁለት ጎሎች ማስቆጠር ሲችል ለሶስተኛዋ የማርሴሎ ጎል ደግሞ ኳሷን በደብል ፖስ አመቻችቶ ማቀበል ሲችል ፤ በጨዋታው ላይ በመቀስ ምት ያስቆጠራት ሁለተኛዋ ጎል በሻምፒዬንስ ሊጉ ታሪክ ከታዬት ማራኪ ጎሎች አንዷ መሆን ችላለች።

ሮናልዶ በተለይ የሁለተኛዋን ጎል በመቀስ ምት ሲያስቆጥር አሰልጣኙ ዘነዲን ዚዳን ማመን ተስኖት ጭንቅላቱን ይዞ የታየ ሲሆን የአሮጊቷ ደጋፊዋች ከመቀመጫቸው ተነስተው አድናቆታቸውን በጭብጨባ ገልፀውለታል።

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በቻምፒዬንስ ሊጉ ታሪክ በ10 ተከታታይ ጨዋታዋች ላይ ጎል ( 16 ጎል ) በማስቆጠር የመጀመሪያ ተጨዋች መሆን ችሏል ፤ በሻምፒዬንስ ሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎሎችም 119 ማድረስ ችሏል ይህም ሮናልዶን የቻምፒዬንስ ሊጉ የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ አድርጎታል።

ሮናልዶ በቻምፒዬንስ ሊጉ በአንድ ክለብ ላይ 9 ጎሎችን ማስቆጠት የቻለ ብቸኛ ተጨዋችም መሆን ችሏል፤ ይህንንም ማድረግ የቻለው ጁቬንቱስ ላይ ነው አሮጊቷ ላይ ከአለፈው አመት የቻምፒዬንስ ሊግ ዋንጫ ጨዋታ ጀምሮ በአጠቃላይ 9 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፤ ከእሱ በመቀጠል ሊዬኒል ሜሲ 8 ጎሎች አርሴናል ላይ ማስቆጠር ችሏል።

Advertisements