ደ ብሩይኔ፣ ሳላህን የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች አድርጎ መረጠ

ኬሸን ደ ብሩይኔ የፕሮፌሽናል እግርኳስ ተጫዋቾች ማህበር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች እንዲሆን ድምፁን ለመሐመድ ሳላህ ሰጥቷል!

ሁለቱ የማንችስተር ሲቲ እና የሊቨርፑል ከዋክብት በዚህ የውድድር ዘመን አስደናቂ ብቃታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ። ደ ብሩይኔ ቡድኑ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት አንድ ጨዋታ ማሸነፍ ብቻ እንዲቀረው ማደርግ ሲችል፣ ሳላህ ደግሞ በአንፊልድ ገና በመጀመሪያ የውድድር ዘመን ቆይተው አስድማሚ ብቃት ማሳየት ችሏል።

የፕሪሚየር ሊጉን የዋንጫ ክብር ለመቀዳጀት በሳምንቱ መጨረሻ ማንችስተር ዩናይትድን ብቻ ማሸነፍ በሚጠበቅበት ሲቲ የዋንጫ ውጤታማነት ምክኒያት ደ ብሩይኔ የኮከብነት ሽልማቱን የመወሰድ ከፍተኛ ዕድል አለው።

ይሁን እንጂ በዚህ የውድድር ዘመን በ31 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ 29 ግቦችን ከመረብ ላይ ያሳረፈው ሳላህ ከቤልጂየማዊው ተጫዋች የአሸናፊነት ድምፅ ተችሮታል!

ተጫዋቾች የራሳቸውን ቡድን ተጫዋች መምረጥ የማይችሉ ቢሆኑም ነገር ግን ደ ብሩይኔ በሚያስገርም ሁኔታ ለኮከብነቱ በዋናነት ለሚፎካከረው ተጫዋች የአሸናፊነት ድምፁን ሰጥቷል።

“ሳላህን መርጫለሁ። አሸናፊነቱ ይገባዋል። አሸናፊው የእኛ ቡድን የሆነ ተጫዋች ካልሆነ እሱ [ሳላህ] ይገባዋል ብዬ አስባለሁ።” ሲል ደ ብሩይኔ ለቢቲ ስፖርት የቴሌቭዥን ጣቢያ ተናግሮ “እኔ ከዚህ በፊት የሆነውን ነገር አልመለከትም። [ምርጫዬ] ከእኛ ቡድን አባል ለአንዱ ካልሆነ ለአሸናፊነቱ ከሳላህ ውጪ እንዴት ሌላ ሰው መምረጥ እንዳለብኝም ማወቅ አያስፈልገኝም። ” ሲልም ጨምሮ ተናግሯል።

ይሁን እንጂ ደ ብሩይኔ ለቶተንሃሙ ሃሪ ኬን እና ለሲቲ የቡድን አጋሩ ዳቪድ ሲልቫ ያለውን ልዩ አድናቆት ሳይገልፅም አልቀረም።

“ሚዛናዊ ነኝ። እሱ ማሸነፍ ካለበት ያሸንፋል። እሱ በዚያ ከኬን፣ ከእኔና ከሲልቫም ይበልጣል። እነዚህ ያለማቋረጥ የዓመቱ አራት ምርጥ ተጫዋቾች ነበሩ። በድምፅ አሰጣጥ ላይ ግን ግልፅ መሆን አለብኝ። እሱ የሚገባው ከሆነ ድምፄን ለእሱ ሰጥቻለሁ። ሌሎች ያን ባያደርጉ እኔ ግድ አይሰጠኝም።”

ሁለቱ ተጫዋቾች ሲቲ ወደአንፊልድ ተጉዞ ዛሬ (ረቡዕ) ምሽት ሊቨርፑልን በሚገጥምበት የሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ እርስ በእርስ ይገናኛሉ።

በዚህ የውድድር ዘመን እስከሁን ሲቲ በኢትሀድ ቀዮቹን 5ለ0 መርታት በቻለበት እና ሊቨርፑል ደግሞ በአንፊልድ 4ለ3 ባሸነፈበት እንዲሁም የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን በዚህ የውድድር ዘመን ሽንፈት ሲገጥመው የመጀመሪያው በሆነበት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ሁለቱ ተጫዋቾች ለሁለት ጊዜያት ያህል ተገናኝተዋል።

ደ ብሩይኔ ለፕሪሚየር ሊጉ የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ድምፁን የሰጠም ሲሆን፣ ምርጫው ያደረገው ደግሞ ባለፈው ክረምት በ42 ሚ.ፓውንድ ከአያክስ ቶተንሃምን የተቀላቀለውን ዳቪንሰን ሳንቼዝን ነበር።

ደ ብሩይኔ በግሉ አስደናቂ የውድድር ዘመን ያሳለፈ ሲሆን፣ በ31 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታም ሰባት ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ በቡድን አጋሮቹ አማካኝነት ግብ መሆን የቻሉ 15 ኳሶችን ደግሞ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

Advertisements