ንዋንኮ ካኑ 2019 ላይ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ለመሆን እንደሚወዳደር አሳወቀ

የቀድሞ የአርሰናል እና የኢንተርሚላን የአጥቂ ተሰላፊ የነበረው ንዋንኮ ካኑ 2019 ላይ በሚደረገው የናይጄሪያ የፕሬዝዳንት ምርጫ ላይ እንደሚወዳደር አሳውቋል።

ጆርጅ ዊሀ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ሆኖ ከተመረጠ በኋላ በሌሎች የቀድሞ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋቾች ላይ መነቃቃትን ፈጥሯል።

በአውሮፓ ስሙን ያገነነው እና ብቸኛው አፍሪካዊ የባሎንዶር አሸናፊው ጆርጅ ዊሀ ከወር በፊት የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ሆኖ ሲሾም የአለም መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

አሁን ደግሞ ናይጄሪያዊው የድሞው የአርሰናል ኮከብ ናይጄሪያን ለመምራት እቅድ እንዳለው አሳውቋል።

ንዋንኮ ካኑ 2019 ላይ በሚደረገው ምርጫ ላይ እንደ ዊሀ ሁሉ ተወዳድሮ ሀገሩን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት መዘጋጀቱን ነው ያሳወቀው።

ከጎል ስፖርት ጋር ቆይታ ያደረገው ካኑ “ዛሬ እዚህ የተገኘሁት ስለሀገራችን የወደፊት ሁኔታ ለመናገር እና ለህዝባችን ደስታ ነው

“ባለፉት 18 ወራት የነበረው አመራር በናይጄሪያ በአንዳንድ መስኮች ላይ ያሽቆለቆለበት በተጨማሪ ደግሞ በሀገሪቷ አጠቃላይ የፀጥታ ችግር እንደነበር ታይቷል

“እኔ እድሉን ባገኝ ነገሮች በተለየ መንገድ እንዲጓዙ አደርጋለው።ለህብረተሰቡም ክብር እና አንድነትን በመመለስ መልካም ነገራችንን ጠብቄ ጥሩ ነገሮችን ወደ ሀገራችን ለመሳብ እሰራለው

“ጆርጅ ዊሀ በላይቤሪያ ማሸነፉ ይህ በኔ በኩል ያለው ህልም እውነት ሊሆን እንደሚችል ጥቆማ ይሰጣል።” ሲል ፍላጎቱን ተናግሯል።

Advertisements