አርሰናል ከ ሲኤስካ ሞስኮ፡ የዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

አርሰናል በዩሩፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ዛሬ ምሽት (ሐሙስ) የሩሲያውን ክለብ ሲኤስካ ሞስኮን በኤመራትስ ስታዲየም ያስተናግዳል።

መድፈኞቹ ትኩረታቸውን በቀጣዮቹ ሳምንታት ከሚያደረጓቸው የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ ወደዚህ በማዞር የዚህን ውድድር ዋንጫ በማንሳት በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ለመቀላቀል ተስፋ በማድረግ ይህን ጨዋታ የሚያደረጉ ይሆናል።


ጨዋታ፡ አርሰናል ከ ሲኤስኬካ ሞስኮ
ቀን፡ ሀሙስ መጋቢት 27፣ 2010 ዓ.ም
ሰዓት፡ ምሽት 4፡05


ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት


በዩናይትድ ስቴትስ በፉቦ ቲቪ እና ፎክስ ስፖርትስ፣ በዩናይትድ ኪንግደም ቢቲ ስፖርት 2፣ ከሰሃራ በታች በአፍሪካ ሱፐር ስፖርት 3፣ በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ ቤን ስፖርት ቴሌቪዥን ቻነሎች ይህን ጨዋታ በቀጥታ መመልከት ይቻላል።

የቡድኖቹ ዜናዎች


አርሰናል

ለመድፈኞቹ መልካም የሆነው ዜና አሌክሳንደር ላካዜቴ በሳምንቱ መጨረሻ ወደመልካም አቋሙ የተመለሰ መሆኑ ነው። ከሳንቲ ካዛሮላ ውጪም አርሰናል ጤናማና የተሟላ የቡድን ስብስብ አለው።

ፒየር-ኤመሪክ አውባምያንግ በዚህ የውድድር ዘመን ለቀድሞ ክለቡ ዶርሙንድ ተሰልፎ የተጫወተ በመሆኑ በዚህ ጨዋታ ላይ ለአርሰናል ተሰልፎ መጫወት የማይችል ተጫዋች ነው።

ሲኤስካ ሞስኮ

ተከላካዩ ኪሪል ናባባኪል በቅጣት ምክኒያት በዚህ ጨዋታ ላይ መሰለፍ የማይችል ተጫዋች ሲሆን፣ ቪክቶር ቫሲን እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ከሜዳ በሚያርቀው የጉልበት ጉዳት በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ ሌላኛው ተጫዋች ነው።

ማሪዮ ፈርናንዴዝ እና አስቴሚር ጎርድዩሼንኮ ደግሞ መሰለፋቸው አጠራጣሪ የሆኑ ተጫዋቾች ናቸው።

የተጫዋቾች ስብስብ፡ አርሰናል፡ ኦስፒና፣ ቼክ፣ ማሲይ፣ ሜርትሳከር፣ ኮሺየልኒ፣ ሆልዲንግ፣ ሞንሪል፣ ሙስታፊ፣ ቻምበርስ፣ ቤለሪን፣ ማቭሮፓኖስ፣ ኮላሲናች፣ ራምሴ፣ ዊልሼር፣ ኦዚል፣ ኢዎቢ፣ ካዛሮላ፣ ዣካ፣ ማይትለንድ-ኒልስ፣ ኤልኒኒ፣ ኔልሰን፣ ሚክሂታሪያን፣ ላካዜቲ፣ ዌልቤክ፣ ኒክሂታህ፣ ዊሎክ

ግምታዊ የመጀመሪያ ተሰላፊዎች፡ ኦስፒና፣ ኮሺየልኒ፣ ሞንሪል፣ ኮላሲናች፣ ቤለሪን፣ ዣካ፣ ዊልሼር፣ ኦዚል፣ ላካዜቲ፣ ዌልቤክ

የተጫዋቾች ስብስብ፡ ፓማዙን፣ አኪኒፊቭ፣ ኪይራንትስ፣ ፈርናንዴስ፣ ኢግናሴቪች፣ ቫሲን፣ አ.ቤሬዙትስኪ፣ ቫ. ቤሬዙትስኪ፣ ሼኒኮቭ፣ ወርንብሉም፣ ሚላኖቭ፣ ዛጎቭ፣ ቪቲንሆ፣ ጎሎቪን፣ ቢስትሮቪች፣ ናችኮ፣ ጎርድዩሼንኮ፣ ኮሶኖቭ፣ ኩሼቭ፣ ሙሳ፣ ቻሎቭ፣ ዝሃማሌትዲኖቭ

ግምታዊ የመጀመሪያ ተሰላፊዎች፡አኪንፊቭ፣ አ. ቤሬዙትስኪ፣ ኢግናሴቪች፣ ቫ. ቤሬዙትስኪ፣ ዌርንብሉም፣ ናባብኪም፣ ኩሼቭ፣ ጎሎቪን፣ ናችኮ፣ ዛጎቭ፣ ሙሳ

Advertisements