የቀድሞው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አምበል ሪያን ዊልንክስ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

Image result for ray wilkins

የቀድሞው የእንግሊዝ እና የቸልሲ ክለብ የሚድፊልድ ተጨዋች የነበረው እንግሊዛዊዬ ሪያን ዊልንክስ በ61 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ዊልንክስ ከቸልሲ በተጨማሪ ለማንችስተር ዬናይትድ ፤ ኤሲ ሚላን ፤ ሬንጀርስ እንዲሁም ኪፒአር ክለቦች መጫወት የቻለ ሲሆን በልብ ኬዝ ምክንያት ለንደን በሚገኘው ሴንት ጆርጅ ሆስፒታል ህይወቱ አልፏል።

ዊልንክስ በቸልሲ እና በእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ውስጥ በተጫዋችነት እንዲሁም በአምበልነት ብሎም በቸልሲ ቤት ውስጥ በምክትል አሰልጣኝነት ማገልገል ችሏል።

ክለቦቹ በቀድሞ ተጨዋቻቸው ህይወት ማለፍ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን የገለፁ ሲሆን የዊልንክስ ቤተሰቦ በተጨዋቹ ሞት ምክንያት ለአፅናኗቸው ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Advertisements