​ጥፋት / ሊቨርፑል ከትናንት ምሽቱ የቻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ጋር በተያያዘ በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ክስ ቀረበበት


ሊቨርፑል ትናንት ምሽት በአስደናቂ ሁኔታ ማንችስተር ሲቲን 3-0 በረታበት የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች ባሳዩት ነውጠኛ ባህሪ የተነሳ በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ክስ ቀርቦበታል፡፡

ክለቡ ከምሽቱ ሁነት ጋር በተያያዘ የደንብ መተላለፍ መዝገብ የተከፈተበት ሲሆን በደጋፊዎቹ ባህሪም የተነሳ በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ህገ ደምብ አንቀፅ 16 ላይ የሚገኙ አራት ደንቦችን ጥሷል የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡ 

የመርሲሳይዱ ክለብ ጥሰት ፈፅሞባቸዋል በሚል ክስ የቀረበበትም ንብረት በማውደም፣ በህብረት ነውጥ በመፈፀም፣ እቃዎችን በመወርወር እና ተቀጣጣይ ቁሶችን በመጠቀም በሚል ነው፡፡

ተቀጣጣይ ቁሶቹን የመጠቀም እና እቃዎችን የመወርወር ክሱ በስታዲየም የተፈፀመ ሲሆን የንብረት ማውደሙና የህብረት ነውጡ ክስ ደግሞ ከስታዲየም ውጪ በማንችስተር ሲቲ መጓጓዣ አውቶብስ ላይ ከተፈፀመ ድርጊት ጋር የተያያዘ ነው፡፡

ሊቨርፑል ከደጋፊዎቹ ድርጊት ጋር በተያያዘ ለሚቀርብበት ክስም ጨዋታውን በሚያዘጋጅበት ወቅት ምንም አይነት እንዝላልነት እንዳልፈፀመ ማስረዳት ካልቻለ ቅጣት ይጠብቀዋል። 

Advertisements