ሙሀመድ ሳላህ የቻምፒዬንስ ሊጉ የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን ተመረጠ

Image result for mohamed salah

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ በመንሀጁል ሀያቲ

 የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጨዋች ሞሀመድ ሳላህ ክሪስቲያኖ ሮናልዶን በማሸነፍ የአውሮፖ ሻምፒዬንስ ሊግ የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች በመባል ተመርጧል።

ግብፃዊዬ ሙሀመድ ሳላህ ሊቨርፑል ከማንችስተር ሲቲ በተደለደለበት የአውሮፖ ቻምፒዬንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ባሳየው ምርጥ አቋም የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

ሳላህ በጨዋታው ላይ በጉዳት ምክንያት በ55ተኛ ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የወጣ ቢሆንም አንድ ጎል እንዲሁም አንድ ጎል የሆነ ኳስ ለቡድን አጋሩ ሰይዶ ማኔ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ሙሀመድ ሳላህ በያዝነው የውድድር አመት በቀዬቹ ቤት አንፀባራቂ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኝ ሲሆን በ41 ጨዋታዋች በ49 ጎሎች ላይ በቀጥታ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

Advertisements