ምኞት / በመጪው ክረምት የጁቬንቱስ ቀዳሚው የዝውውር ኢላማ አንቶኒ ግሪዝማን መሆኑ ተገለፀ


ጁቬንቱስ በመጪው ክረምት ቀዳሚ የዝውውር ኢላማው አንቶኒ ግሪዝማን መሆኑ ተገልጿል።

በቻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በሪያል ማድሪድ 3-0 የተረታው ጁቬንቱስ በሀገር ውሰጥ ያለውን ስኬት በአውሮፓ መድረክ መድገም ከፈለገ በስብስቡ ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚስፈልገው ተረድቷል፡፡ 

ከዚህ ጋር በተያያዘም ለውጡን በአትሌቲኮ ማድሪዱ የፊት መስመር ኮከብ አንቶኒ ግሪዝማን ለመጀመር ማቀዱን ኮሪየር ዴሎ ስፖርት ፅፏል፡፡ 

ፈረንሳዊው አጥቂ ባሳለፍነው ዓመት ስሙ በተደጋጋሚ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ሲያያዝ የሰነበተ ቢሆንም ክለቡ እስካለፈው ጥር የዝውውር መስኮት ድረስ ተጫዋች እንዳያዘዋውር እገዳ ተጥሎበት ስለነበር ወደ እንግሊዝ ከማምራት ይልቅ በአትሌቲኮ ማድሪድ መቆየትን ምርጫው ማድረጉ አይረሳም፡፡

በሌላ በኩል ግን የእንግሊዙ ዘሰን ጋዜጣ ከሰሞኑ እንደፃፈው ግሪዝማ የረጅም ጊዜ አጥብቆ ፈላጊውን ዩናይትድ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ከወዲሁ ከባርሴሎና ጋር ውል መፈራረሙ ተነግሯል። 

ግሪዝማንን ለማዘዋወር የውል ማፍረሻውን 100 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 88 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል የተዘጋጀ ክለብ ፈረንሳዊውን አጥቂ በእጁ ማስገባት ይችላል።  

Advertisements