ኤቨርተን ከ ከሊቨርፑል፡ የመርሲሳይድ ደርቢ ቅደመ ቅኝት

ቀዮቹ ረቡዕ ምሽት በአንፊልድ የፕሪሚየር ሊጉን መሪ ማንችስተር ሲቲን 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ አስደናቂ ብቃታቸውን ማሳየት ችለዋል። ድሉም በሚቀጥለው ሳምንት ከሚያደረጉት የመልስ ጨዋታ በፊት ወደግማሽ ፍፃሜው አንድ እግራቸውን ማሻገር እንዲችሉ አድርጓቸዋል።

የየርገን ክሎፑ ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ ባደረገው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በሳዲዮ ማኔ እና መሐመድ ሳላህ ግቦች ክሪስታል ፓላስን 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። መሐመድ ሳላህም በዚህ የውድድር ዘመን ያስቆጠራቸውን አጠላይ ግቦች 38 አድርሷል። በዚህ ላይ የትኛውም ክለብ ቀዮቹ ማስቆጠር የቻሏቸውን ያህል (37) ከሜዳው ውጪ ከፍተኛ ግብ ማስቆጠር አልቻለም።

ኤቨርተኖች ባለፈው ሳምንት በሜዳቸው በሙሉ የጨዋታ ብልጫ በማንችስተር ሲቲ የደረሰባቸውን የ3ለ1 ሽንፈት ተከትሎ የበፕሪሚየር ሊጉ በ9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ሁለቱ ክለቦች ባለፈው ታህሳስ ወር በአንፊልድ ያደረጉትን የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ 1ለ1 አጠናቀዋል። በዚህ ጨዋታ መሐመድ ሳላህ ሊቨርፑልን ቀዳሚ ያዳረገች ግብ ማስቆጠር ቢችልም፣ ዋይኒ ሩኒ በፍፁም ቅጣት ምት ኤቨርተንን አቻ አድርጓል።

በዚህ የውድድር ዘመን ሊቨርፑል በኤፍኤ ዋንጫ ሶስተኛ ዙር በጄምስ ሚልነር እና ቪርጂል ቫንዳይክ ግቦች 2ለ1 በመርታት ኤቨርተንን ከውድድሩ ውጪ አድርጓል። የኤቨርተንን ብቸኛ ግብ ደግሞ ጊይልፍ ሲጉርድሰን አስቆጥሯል።

የክለቦቹ ዜናዎች


ኤቨርተን

አሽሊ ዊሊያምስ የነበረበትን ቅጣት በላፈው ሳምንት በማጠናቀቁ በዚህ ጨዋታ ላይ ወደሜዳ ይመለሳል።

ኢድሪስ ጉዬ ከነበረበት የጡንቻ ጉዳት አገግሞ የሚመለስ ሌላኛው የኤቨርተን ተጫዋች ቢሆንም፣ ማሰን ሆልጋት ግን አሁንም በቁርምጭሚት ጉዳት ከሜዳ እንደራቀ ይቆያል።

ጊይልፍ ሲጉርድሰን፣ ኢላኪዩም ማንጋላ እና ጄምስ ማካርቲ ደግሞ ለረጅም ጊዜያት ከሜዳ እንደራቁ የሚቆዩ ተጫዋቾች ናቸው።

ሊቨርፑል

በረቡዕ ምሽቱ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ላይ ትልቅ ዜና የነበረው የሞ ሳላህ ጨዋታውን አቋርጦ የመውጣት ጉዳይ ነበር። ግብፃዊ ተጫዋች የብሽሽት ጉዳት ሳይገጥመው እንደማይቀርም ተፈርቶ ነበር። ነገር ግን የተጫዋቹን በዚህ ጨዋታ ላይ የመሰለፍ ወይም ያለመሰለፍ ሁኔታ በትዕግስት እየጠበቁ ስለመሆናቸው የርገን ክሎፕ ተናገረዋል።

ያም ሆነ ይህ ግን ቀዮቹ በቀጣዩ ሳምንት ላለባቸው ወሳኝ የሻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታ ሲሉ የክንፍ ተጫዋቹን በዚህ ጨዋታ ላይ ላያሰልፉት ይችላሉ።

ኤምሬ ቻን ዛሬው ጨዋታ ላይ ወደሜዳ ሊመለስ ይችላል። ነገር ግን ጆ ጎሜዝ እና አዳም ላላና አሁንም ካለባቸው ጉዳት ያላገገሙ ተጫዋቾች ናቸው።

ናትናኤል ክላይን ገጥሞት ከነበረው የረጅም ጊዜ ጉዳት አገግሞ የሚገኝ ቢሆንም፣ የቀድሞ ብቃቱን ግን ሙሉ ለሙሉ መልሶ ማግኘት የቻለ አይመስልም።

ዦል ማቲፕ ደግሞ በገጠመው ጉዳት እስከዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ ድረስ ወደሜዳ የማይመለስ ተጫዋች ነው።

ግምታዊ አሰላለፎች


ሊቨርፑል

ኤቨርተን

Advertisements