የቻምፒዬንስ ሊጉ ሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ምርጥ 11

 

Image result for champions league

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ በመንሀጁል ሀያቲ

የሻምፒዬንስ ሊጉ የመጀመሪያ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዋች ተጠናቀዋል ሪያል ማድሪድ ፤ ሊቨርፑል ባርሳ እንዲሁም ባየር ሙኒክ በተፎካካሪዋቸው ላይ ሶስት እና ከሶስት በላይ ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል፤የሩብ ፍፃሜው የመጀመሪያው ዙር ያልተጠበቁ ውጤቶች እንዲሁ በግርምት አፍ የሚያሲዙ በጣም አስገራሚ የሆኑ ምርጥ ጎሎችን ያየንበት አስገራሚ ሳምንት ነበር። ከቻምፒዬንስ ሊጉ ሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ምርጥ 11 እንደሚከተለው አስቀምጠንላችሆል ፡፡

ግብ ጠባቂ ኬለር ናቫስ ( ሪያል ማድሪድ ) ኬለር ናቫስ በጨዋታው ላይ ጎሎን ሳያስደፍር መውጣት የቻለ ሲሆን፤ የተመቱበትን ሹቶች እንዲሁም አርጀንቲናዊዬ አጥቂ ሄጊዬን በጣም ለጎል የቀረበ ሙከራ በጭንቅላቱ የገጫትን ኳስ ማዳን ችሏል። በተጨማሪም ፖውሎ ዲባላ ያቀኛትን የቅጣት ምት እንዲሁ ማዳን የቻለ ሲሆን የሳምንቱ ምርጥ በረኛ በመሆን ተመርጧል።

የቀኝ መስመር ተከላካይ አሌክሳንደር አርኖልድ ( ሊቨርፑል)

አርናልድ በጣም የተዋጣለት ጨዋታ ሲጫወት ነበር በተለይ የማንችስተር ሲቲ ቁልፍ የማጥቃት አቅም በጣም ማቆም ችሎ ነበር፤ ልጁ በተለይ በእድሜው ትንሽ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ትችቶች ያስተናግድ ነበር በጨዋታው ላይ የተችዋቹን አፍ ማዘጋት የቻለ አቋም ማሳየት ችሏል።

ቁጥሮች ፦ ኳሶችን ከአደጋ ክልል በማስወገድ (10 ) እና ኳሶችን በማጨናገፍ (7) ከሁሉም የሊቨርፑል ተጨዋቾች የበላይነትን መውስድ ችሏል።

መሀል ተከላካይ ጀራርድ ፒኬ ( ባርሴሎና )

ፒኬ በጨዋታው ላይ የአለማችን ምርጡ የመሀል ተከላካይ መሆኑንን በድጋሚ በኤዲን ዜኮ እና ክለቡ ሮማ ላይ በድጋሚ ማሳየይ ችሏል፤ የባርሴሎና አጥቂዋች ምርጥ ባልሆኑበት ምሽት ምርጥ አቋም ማሳየት ችሏል ጎልም በስሙ አስመዝግቧል።

ቁጥሮች ፦ ፒኬ 5 ኳሶችን ከአደጋ ክልል በማስወገድ ሲችል 4 እርስ በእርስ ግንኙነቶችን ማሸነፍ ችሏል ይህም በሜዳ ውስጥ ካሉት ሁሉ ተጨዋቾች ቀዳሚ ያደርገዋል።

 

መሀል ተከላካይ ዲያን ሎቭረን ( ሊቨርፑል)

ክሮሺያዊዬ የመሀል ተከላካይ ሎቭረን ለቨርጂል ቫንዳይክ ምርጥ አጣማሪ እንደሆነ ያሳየበት ምሽት ነበር ፤አንድ ለአንድ የተገኛኘባቸውን አጋጣሚዋች በሙሉ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በጥልቀት ኳሶችን ለአጥቂዋች በማድረስ ሲረዳ ነበር።

የግራ መስመር ተከላካይ ማርሴሎ ( ሪያል ማድሪድ )

ብራዚላዊዬ ተከላካይ ለቡድኑ ጎል ከማስቆጠሩም በላይ ኳሶችን ድሪብል ሲያደርግ አስገራሚ ነበር። ቁጥሮች ፦ ማርሴሎ 80 ጊዜ ከኳስ ጋር ንክኪ ሲያደርግ ይህም ከየትኛውም የጁቬንቱስ ተጨዋች በላይ ያደርገዋል። የመሀል አማካኝ ፡ ጀምስ ሚልነር ( ሊቨርፑል ) የሊቨርፑሉ የመሀል አማካኝ ሚልነር በዚህ የውድድር ዘመን በቻምፒዬንስ ሊጉ 7 ኳሶችን አሲስት በማድረግ ቀዳሚው ተጨዋች መሆን ችሏል።

ቁጥሮች ፦ ብዙ ኳሶችን በማስጣል (5 ) ከሁሉም የሊቨርፑል ተጨዋቾች ቀዳሚ መሆን ችሏል።

የመሀል አማካኝ ኢቫን ራኪቲች ( ባርሴሎና)

ራኪቲች የተሳኩ ቅብብሎችን በማድረግ ከሁሉም ተጨዋቾች ቀዳሚ ነው ፤ እሱ ጎል ማስቆጠር ባይችልም ጠንካራ ጫና ሲያደርግ ነበር ቁጥሮች ፦ 77 የተሳኩ ቅብብሎችን ማድረግ የቻለ ብቸኛው ተጨዋች ነው።

የመሀል አማካኝ ቶኒ ክሮስ ( ሪያል ማድሪድ )

ጀርመናዊዬ የመሀል አማካኝ በጁቬንቱስ ላይ አስገራሚ የሆነ የጎል ሙከራ ማድረግ ችሎ ነበር ነገር ግን የፖሉ የላይኛው አግዳሚ መልሶበታል፤ ሚድፊልዱን ጥሩ መቆጣጠር የቻለ ሲሆን የኳስ ንኪኪው በፐርሰንት 96% ነበር።

የቀኝ ክንፍ ሙሀመድ ሳላህ ( ሊቨርፑል )

ጎል ማስቆጠር ቻለ፤ ለጎል የሚሆን ኳስ ማቀበል ቻለ፤ ተቀይሮ እስከ ወጣበት ደቂቃ ድረስ የሊቨርፑልን የማጥቃት ሀይል በደንብ ተጭኖ እንዲጫወት ማገዝ ችሏል። ቁጥሮች ፦ በቻምፒዬንስ ሊጉ 7 ጎሎችን ማስቆጠር ሲችል 9 ኳሶችን ማቀበል ችሏል። የግራ ክንፍ : ፍራንክ ሪቤሪ ( ባየርን ሙኒክ) ፈረንሳያዊዬ ኮከብ ጨዋታውን ሙሉ ለሙሉ መቀየር ችሏል፤ 1 ለ 0 ሲመራ የነበረውን ቡድኑን ወደ 2 ለ 1 አሸናፊነት መቀየር ችሏል። ቁጥሮች ፦ ድሪብል የሚያደርጋቸው ኳሶች 100% የተሳኩ ነበሩ ፤ ለጎል የሚሆኑ እድሎችን ( 5) መፈጠር ችሏል ።

አጥቂ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ( ሪያል ማድሪድ )

ስለዚህ ሰው ምን ማለት ይቻላል? ብዙዋች በጁቬንቱስ ሜዳ ላይ ጎሎችን ማስቆጠር ይቸገራሉ እሱ ግን ይህንን ማድረግ ችሏል፡ በተለይ ሁለተኛዋ ጎል አድናቂዋቹን ብቻ ሳይሆን አለምን በግርምት አፍን ያሲያዘች ጎል ማስቆጠር ችሏል ፤ ለቡድን አጋሩ ለጎል የሆነች ኳስ ማቀበል ችሏል።

ቁጥሮች ፦ በቻምፒዬንስ ሊጉ ታሪክ በ10 ተከታታይ ጨዋታዋች ላይ ጎል በማስቆጠር የመጀመሪያ ተጨዋች መሆን ችሏል።

 

Advertisements