ማን ሲቲ ከ ማን ዩናይትድ፡ የማንችስተር ደርቢ ቅደመ ዳሰሳ

ማንችስተር ሲቲዎች በዛሬ ምሽቱ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድን ማሸነፍ የሚችሉ ከሆነ የዚህ የውድድር ዘመን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆናቸውን በማረጋገጥ በሳምንቱ አጋማሽ በሻምፒዮንስ ሊጉ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በሊቨርፑል የደረሰባቸውን ሽንፈት የሚዘነጉበት ይሆናቸዋል

በሌላ በኩል ዩናይትዶች የከተማ ቀንደኛ ተቀናቃኞቻቸውን የፕሪሚየር ሊግ ድል (የማይሆን ቢመስልም) ቢቻላቸው ጨርሶ ለማጨናገፍ ካልሆነ ደግሞ የዋንጫ አሸናፊነታቸውን ቢያንስ በአንድ ጨዋታ ለማዘግየት በማሰብ ይህን ጨዋታ የሚያደርጉ ይሆናል።

የጨዋታ ቅድመ ቅኝት


የጋርዲዮላው ቡድን የዚህን የውድድር ዘመን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ለማንሳት በዋንጫው ጫፍ ላይ ይገኛል። ሙሉ ለሙሉ የዋንጫውን እጀታ ማንሳቱን ለማረጋገጥ ግን ይህን ከከተማ ተቀናቃኙ ጋር የሚያደረገውን ጨዋታ ማሸነፍ ይጥበቅበታል።

ረቡዕ ምሽት በሻምፒዮንስ ሊጉ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በአንፊልድ በውድድር ዘመኑ ለሁለተኛ ጊዜ ሽንፈት የደረሰበት የጋርዲዮላው ቡድን አሁን ከተከታዩ ዩናይትድ 16 ነጥቦችን ከፍ ብሎ ወደሚገኝበት ፕሪሚየር ሊግ ትኩረቱን አድርጓል።

ጨዋታው የማንችስተር ደርቢ እንደመሆኑ በሁለቱም ክለቦች ዘንድ ያለው የመሸናነፍ ስሜት በእጅጉ ከፍ ያለ ነው። በመሆኑም ዩናይትዶች በኢትሃድ ጎረቤቶቻቸው የዋንጫ አሸናፊነት የደስታ ጮቤ ሲረግጡ መመልከትን ፈፅሞ አይፈልጉም።

በታህሳስ ወር በኦልትራፎርድ በተደረፈው የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸው በዴቪድ ሲልቫና ኒኮላስ ኦታሜንዲ ግብ የጋርዲላው ቡድን ዩናይትድን ማሸነፍ ችሏል።

የክለቦቹ ዜናዎች


ማንችስተር ሲቲ

ሰርጂዮ አጉዌሮ ገጥሞት ከነበረው ጉዳት አገግሞ በዚህ ጨዋታ ወደሜዳ ሊመለስ ይችላል።

ቤንጃሚን ሜንዲ ከገጠመው የረጅም ጊዜ ጉዳት አገግሞ ወደጨዋታ ለመመለስ ዝግጁ ቢሆንም፣ ከማንችስተር ጋር በሚደረገው በዚህ ጨዋታ ላይ ግን የሚሆን አይመስልም።

ማንችስተር ዩናይትድ

በዩናይትድ በኩል ፊል ጆንስ ምንም እንኳ ገጥሞት ከነበረው ጉዳት ለመመለስ ዝግጁ ቢሆንም ለደርቢው ጨዋታ መሰለፉ ግን አጠራጣሪ ነው።

ይሁን እንጂ ሰርጂዮ ሮሜሮ እና ዳሊ ብሊንድ ባለባቸው ጉዳት አሁንም ከሜዳ እንደራቁ ይቆያሉ።

ግምታዊ አሰላለፎች


ማንችስተር ሲቲ

ማንችስተር ዩናይትድ

Advertisements