አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ሪያል ማድሪድ| የማድሪድ ደርቢ ቅድመ ዳሰሳ

ሪያል ማድሪድ እና የከተማ ተቀናቃኙ አትሌቲኮ ማድሪድ በላ ሊጋው የሁለተኝነትን ደረጃ ለመያዝ የሚደረገውን ፉክክር በአሸናፊነት ለመወጣት ሲሉ እሁድ አመሻሹ ላይ በበርናባዩው ይፋለማሉ።

ሎስ ሮኺብላንኮዎቹ በዚነዲን ዚዳኑ ቡድን ላይ የአራት ነጥቦች የበላይነቱን ይዘው ካለፉት 22 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊጉን በሁለተኝነት ለማጠናቀቅ በማሰብም ይህን ጨዋታ የሚያርጉ ይሆናል።

የቡድኖቹ ዜናዎች


ሁለቱም ክለቦች በሳምንቱ አጋማሽ በአውሮፓ ውድድሮች ላይ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ያለባቸው በመሆኑ በሁለቱ ክለቦች መካከል የሚደረገው ጨዋታ ክብደትና ቅለት አሰልጠኞቻቸው በየግላቸው በሚኖራቸው የተጫዋቾች ምርጫ ላይ የተመሰረተ ይሆናል።

ሉካስ ቫስኬዝ፣ ጋርዝ ቤል እና ማርኮ አሰንሲዮ በባለሜዳው ክለብ በኩል የመጀመሪያ ተሰላፊነት ሚና ሊኖራቸው የሚችሉ ተጫዋቾች ሲሆኑ፣ ናቾ ፈርናንዴዝ ባለፈው ሳምንት በደረሰበት ጉዳት ምክኒያት በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ነው።

ኬቨን ጋሜሮ እና ፈርናንዶ ቶሬ በእንግዳው ቡድን በኩል ሊሰለፉ የሚችሉ ተጫዋቾች ቢሆኑም ፊሊፔ ልዊዝ ግን እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ ጉዳት የገጠመው በመሆኑ በዚህ ጨዋታ ላይ አይሰለፍም።

ስለጨዋታው ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦች


  • ዚነዲን ዚዳን በአሰልጣኝነት ዘመኑ ባለፉት አራት የላ ሊጋ ጨዋታዎች አራት ጊዜ አሸንፎ በአንዱ ደግሞ በአቻ ውጤት ማጠናቅቅ የቻለውን የዲያጎ ሲሞኒውን አትሌቲኮ ማድሪድን በበርናቢዩው ፈፅሞ ማሸነፍ ችሎ አያውቅም።
  • ይህ ጨዋታ ባለፉት ሶስት ዓመታት በሁለቱ ክለቦች መካከል የሚደረግ አስራሁለተኛ ጨዋታ ሲሆን፣ ይህ ጨዋታ ግን በሁለቱ ክለቦች መካከል የተቀራረበ ነጥብ ኖሮ የሚደረግ ይሆናል።
  • የአትሌቲዎች የተከላካይ ክፍል በእጅጉ ጠንካራ ሲሆን፣ በበርናቢዩው ባደረጓቸው ያለፉት አራት ጨዋታ ላይ የተቆጠረባቸው ግብ ሁለት ብቻ ነበር።
  • አትሌቲኮዎች በአዲሱ ስታዲየማቸው በዋንዳ ሜትሮፓሊታኖ ባለፈው ህዳር ወር ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት የደርቢ ጨዋታ ሁለቱ ክለቦች ያለግብ ያጠናቀቁ ከመሆኑም በላይ ሁለቱም ክለቦች በድምሩ ወደግብ ያደረጉት ሙከራ አራት ብቻ ነበር።

ግምታዊ አሰላለፎች


አትሌቲኮ ማድሪድ

ናቫስ፣ ካርቫኻል፣ ቫራን፣ ራሞስ፣ ማርሴሎ፣ ሞድሪች፣ ኮቫቺች፣ ክሩዝ፣ አሰንሲዮ፣ ቤል፣ ሮናልዶ

አትሌቲኮ ማድሪድ

ኦብላክ፣ ኹዋንፍራን፣ ጎዲን፣ ሳቪች፣ ሉካስ፣ ሳኡል፣ ጋቢ፣ ኮኬ፣ ኮሬያ፣ ፍሪዝማን፣ ኮስታ

Advertisements