ፋቢዬ ካፔሎ ከአሰልጣኝነት ስራቸው ጡረታ መውጣታቸውን ይፋ አደረጉ

በስድስት ሀገራት ከ30 አመታት በላይ የአሰልጣኝነት ቆይታ በማድረግ ብዛት ያላቸውን ድሎችን የተጎናፀፉት አንጋፋው አሰልጣኝ ፋቢዬ ካፔሎ ከአሰልጣኝነት ስራቸው ጡረታ መውጣታቸው አሳወቁ።

ካፔሎ የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው እንደሚሾሙ በሚጠበቁበት ወቅት በቻይና ያደረጉት ቆይታ የመጨረሻቸው መሆኑ እና ከአሰልጣኝነት ስራቸው ጡረታ መውጣታቸው አሳውቀዋል።

ካፔሎ በተለይ በሚላን እና በማድሪድ ውጤታማ ቆይታ የነበራቸው ሲሆን ከሮሲነሪዎቹ ጋር በ 1994 የቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫን ጭምር ማንሳት ችለው ነበር።

2001 ላይ ከሮማ ጋርም የሴሪ ኣ ዋንጫ ካነሱ በኋላ ከጁቬንቱስ ጋር ሁለት ጊዜ የዋንጫ ባለቤት ቢሆኑም በጨዋታ ውጤት ማጭበርበር ከአሮጊቷ ጋር ያነሱት ዋንጫ ተሰርዞባቸዋል።

ከጂያንግሱ ሰኒንግ ጋር በቅርቡ የተለያዩት ካፔሎ የጣሊያን ብሔራዊ ቡድንን ለመረከብ ፍላጎት እንደሌላቸው በማሳወቅ ረጅም አመት ከቆዩበት ስራቸው ጡረታ መውጣታቸው አሳውቀዋል።

ካፔሎ በሚላን

“ከራሺያ እና ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር አብሬ ሰርቻለው።ክለብም በድጋሚ የማሰልጠን ፍላጎት የነበረኝ ሲሆን ጂያንግሱም የመጨረሻዬ ሆኗል።የፈለኩትን ሁሉ መስራት ችያለው።

“እስካሁን ድረስ በሰራሁት ነገር ደስተኛ ነኝ።አሁንግን የእግርኳስ ተንታኝ እሆናለው።”

“በቻይና የነበረኝ ልምድ በጣም አስደሳች ነበር።ለመግባባት ከባድ ቢሆንም የተለየ አይነት ኳስ ይጫወታሉ።ሁልጊዜም አስተርጓሚ ያስፈልገኝ ነበር።” በማለት ተናግረዋል።

Advertisements