ስርዓት አልበኝነት / የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በፔፕ ጋርዲዮላ ላይ ክስ አቀረበ

የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ከትናንት ምሽቱ የሊቨርፑል የ 2-1 ድል ጋር በተያያዘ በማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ላይ ሁለት የደምብ ጥሰት ክሶችን አቅርቧል። 

ከኢትሀዱ ክለብ በተጨማሪም ደጋፊዎቹ በፈፀሙት የሁከት እና ረብሻ ድርጊት ምክንያት በእግር ኳስ ማህበሩ ክስ የቀረበበት ሊቨርፑል ቅጣት ይጠብቀዋል።

ጋርዲዮላ ክስ የቀረበባቸው በሁለት ድርጊቶች ሲሆን የመጀመሪያው ሊሮይ ሳኔ ያስቆጠረው ግብ ከጨዋታ ውጪ በሚል ሲሻር ተቃውሞ ማሰማታቸው ነው።

ሁለተኛው ድርጊት ደግሞ ጋርዲዮላ ቀይ ካርድ ተመልክተው ሳለ የማህበሩን ህገ ደምብ አንቀፅ 69 በመጣስ ተቀያሪ ወንበር ከሚገኙ የስብስባቸው አባላት ጋር ግንኙነት መፍጠራቸው እና መነጋገራቸው ነው። 

በኢትሀዱ አለቃ ላይ የቀረበው ክስ በመጪው ግንቦት ወር መጨረሻ በማህበሩ የቁጥጥር፣ ስነምግባር እና ስነስርዓት ክፍል ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል። 

Advertisements