ጣሊያን በዓለም የሃገራት የእግርኳስ ደረጃ መጥፎ የሚባል የውጤት መንሸራተት ገጠማት

ጣሊያን ለሩሲያው የዓለም ዋንጫ መብቃት ሳትችል ከቀረች ወዲህ በፊፋ የዓለም ሃገራት የእግርኳስ ደረጃ የምንጊዜውም መጥፎ በሚባል ሁኔታ ወደ20ኛ እንድትንሸራተት ሆናለች።

አዙሪዎቹ ከስዊድን ጋር ባደረጉት የዓለም ዋንጫ የደርሶ መልስ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ተሸንፈው ለውድድሩ ማለፍ ሳይችሉ ቀርተው ደረጃቸው ወደ14ኛ ዝቅ ካለ ወዲህ ወዲህ በወዳጅነት ጨዋታዎች በአርጄንቲና 2ለ0 ሲሸንፉ ከእንግሊዝ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ ደግሞ 1ለ1 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል።

ለአራት ጊዜያት ያህል የዋንጫ ባለቤት መሆን የቻለችው ጣሊያን ከዚህ ቀደም የነበራት መጥፎ የሚባል የደረጃ መንሸራተት በ2015 እና በ2017 ወደ17ኛ ደረጃ ዝቅ ያለችበት ነበር።

በወሩ የፊፋ የዓለም ሃገራት ደረጃ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ጀርመን ብራዚልን ቀድማ በቀዳሚነት መቀመጧን ስትቀጥል ቤልጂየም ደግሞ ፓርቱጋልን እና አርጄንቲናን አልፋ በሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች።

Advertisements