የእንግሊዝ የፕሮፌሽናል እግርኳስ ማህበር የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ለመለየት ስድስት እጩዎች ታወቁ

በየአመቱ ይፋ የሚደረገው የእንግሊዝ የፕሮፌሽናል እግርኳስ ማህበር የአመቱ ምርጥ ተጫዋችን ለመለየት ስድስት ተጫዋቾች እጩ ሲሆኑ ዴቪድ ዲህያ አንዱ እጩ ውስጥ የተካተተ ሆኗል።

ሻምፕዮን ለመሆን ከተቃረበው ማን ሲቲ ሶስት ተጫዋች የተመረጡ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ መሀመድ ሳላህ፣ ዴቪድ ዴሂያ እና ሀሪ ኬን እጩ ውስጥ ተካተዋል።

አሸናፊው ከመሀመድ ሳላህ እና ከኬቨን ዴብሩይን እንደማይወጣ እየተነገረ ሲሆን ከሁለቱ ተጫዋቾች ግን ማን ክብሩን ሊቀዳጅ እንደሚችል ጊዜ የሚፈታው ሆኗል።

ዴብሩይን ለሲቲ የአመቱ የሻምፕዮንነት ጉዞ ጉልህ ሚና በመጫወት ድንቅ አመትን አሳልፏል።

ተጫዋቹ 15 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማመቻቸት ቅድሚያውን የያዘ ሲሆን ሰባት ጎሎችንም በስሙ አስመዝግቧል።

መሀመድ ሳላህ በበኩሉ በግሉ የፕሪምየርሊጉን ከፍተኛ የጎል አግቢን እየመራ ይገኛል።

ተጫዋቹ በመጀመሪያ አመቱ 29 ጎሎችን ሲያስቆጥር ለ 9 ጎሎች መቆጠር ደግሞ ምክንያት ሆኗል።ቡድኑንም በሩብ ፍፃሜ በደርሶ መልስ ሊቨርፑል ላይ ጎል በማስቆጠር ወደ ግማሽ ፍፃሜው እንዲያቀኑ አግዟል።

ሀሪ ኬንም እንዲሁ ስፐርሶች በቀጣይ አመት በቻምፕየንስ ሊግ ላይ ለመሳተፍ እያደረጉት ያሉት ሩጫ ላይ ጎሎችን በማስቆጠር ከሳላህ በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የሳኔ እና የሲልቫ ሚናም ሲቲዎች ለነበራቸው የአመቱ ድንቅ አቋም ስማቸው ሳይጠቀስ የማይታለፉ ሲሆን የማን ዩናይትዱ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሂያ ደግሞ አስደናቂ ኳሶችን በማዳን ቡድኑን በተደጋጋሚ ሲታደገው ተስተውሏል።

የቀድሞ ተጫዋቾች ምን አሉ?

ፍራንክ ላምፓርድ

“እኔ አንድ ስም ጥራ ብባል የምጠራው ኬቨን ዴብሩይን ነው።ምክንያቱም እሱ የሲቲ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ቆይቷል፣ሻምፕዮን ለሚሆነው ቡድንም በጣም ተፅእኖ ፈጣሪ ነበር”

የቀድሞ የሲቲ ተጫዋች ሌስኮት

“ለመምረጥ ከባድ ነው ነገርግን ዴብሩይን የተሻለ ነው።ምክንያቱም ሲቲን የሊጉን ዋንጫ እንዲያሸንፍ አድርጓል።”

አለን ሺረር

“የኔ አሸናፊ ሞ ሳላህ ነው።ከዚህ በፊት እንዳልኩት የቻምፕየንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ሁለቱን ተጫዋቾች የለየሁበት ነው።በሁለቱ ጨዋታዎች ሳላህ ሲቲ ላይ ጎል በማግባት ቡድኑ ወደ ግማሽ ፍፃሜ እንዲገባ አግዟል።”

እናንተስ ምርጫችሁን ለማን ትሰጣላችሁ?ዴብሩይን ወይስ ሳላህ?

Advertisements