ባየር ሙኒክ ከ ሪያል ማድሪድ፡ የከዚህ ቀደም ግንኙነታቸው እና ስለድልድሉ የተሰጡ አስተያየቶች

ባየር ሙኒክ በሩብ ፍፃሜው ሲቪያን በደርሶ መልስ 2ለ1 እና ሪያል ማድሪድ ጁቬንቱስን 4ለ3 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለሻምፒዮንስ ሊጉ የግማሽ ፍፃሜ የደርሶ መልስ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ተፋላሚ መሆናቸው አርብ ዕለት በወጣው የዕጣ ድልድል ተረጋግጧል።

ተከታዩ ፅሁፍም ሁለቱ ክለቦች በአውሮፓ አበይት ውድድሮች ላይ የነበራቸውን ግንኙነት ዝርዝር ጨዋታ በቁጥራዊ መርጃ እስደግፎ የሁለቱ ክለቦችን የዕጣ ድልድል ይመለከታል።

ጨዋታው መቼ ይደረጋል?

የመጀመሪያው ጨዋታ፡ ረቡዕ ሚያዝያ 17፣ 2010 ዓ.ም
የመልሱ ጨዋታ፡ ረቡዕ ሚያዝያ 23፣ 2010 ዓ.ም


የከዚህ ቀድም የአውሮፓ መድረኮች የእርስ በርስ ግንኙነቶቻቸው

ተጫወቱ: 24
ባየር ሙኒክ: 11 (ግቦች 36)
ሪያል ማድሪድ: 11 (ግቦች 37)
አቻ: 2

1975/76 የአውሮፓውያኑ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ

ማድሪድ 1-1 ባየር
ባየር 2-0 ማድሪድ
በድምሩ: 3-1 ባየር አሸነፈ

1986/87 የአውሮፓውያኑ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ

ባየር 4-1 ማድሪድ
ማድሪድ 1-0 ባየር
በድምሩ: 4-2 ባየር አሸነፈ

1987/88 የአውሮፓውያኑ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ

ባየር 3-2 ማድሪድ
ማድሪድ 2-0 ባየር
በድምሩ: 4-3 ማድሪድ አሸነፍ

1999/2000 የሻምፒዮንስ ሊግ ሁለተኛ የምድብ ማጣሪያ

ማድሪድ 2-4 ባየር
ባየር 4-1 ማድሪድ
በድምሩ፡ 8-3 ባየር አሸነፈ

1999/2000 ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ
ማድሪድ 2-0 ባየር
ባየር 2-1 ማድሪድ
በድምሩ: 3-2 ማድሪድ አሸነፈ

2000/01 ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ
ማድሪድ 0-1 ባየር
ባየር 2-1 ማድሪድ
በድምሩ: 3-1 ባየር አሸነፈ

2001/02 ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ
ባየር 2-1 ማድሪድ
ማድሪድ 2-0 ባየር
በድምሩ: 3-2 ማድሪድ አሸነፈ

2003/04 ሻምፒዮንስ ሊግ 16ቱ ዙር
ባየር 1-1 ማድሪድ
ማድሪድ 1-0 ባየር
በድምሩ: 2-1 ማድሪድ አሸነፈ

2006/07 ሻምፒዮንስ ሊግ 16ቱ ዙር
ማድሪድ 3-2 ባየር
ባየር 2-1 ማድሪድ
በድምሩ: 4-4 ባየር፣ ከሜዳ ውጪ ባገባ አሸንፈ

2011/12 ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ
ባየር 2-1 ማድሪድ
ማድሪድ 2-1 ባየር
በድምሩ፡ 3-3፣ ባየር በፍፁም ቅጣት ምት አሸነፈ

2013/14 ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ
ማድሪድ 1-0 ባየር
ባየር 0-4 ማድሪድ
በድምሩ: 5-0 ማድሪድ አሸነፈ

2016/17 ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ
ባየር 1-2 ማድሪድ
ማድሪድ 4-2 ባየር
በድምሩ፡ 6-3 ሪያል ማድሪድ አሸነፈ


የጨዋታው እውነታዎች

  • በሁለቱ ክለቦች መካከል የሚደረገው የሚያዝያ 17ቱ የመጀመሪያ ጨዋታ በሻምፒዮንስ ሊጉ የግማሽ ፍፃሜ ሰባተኛ ጨዋታቸው ይሆናል። ይህም በውድድሩ ላይ ይህን ያህል ጊዜ በመገናኘት ቀዳሚ ክለቦች ያደረጋቸዋል። በዚህ ደረጃም ባየር አራት ጊዜ ሲያሸንፍ ማድሪድ ደግሞ ሁለት ጊዜ ማሸነፍ ችሏል።
  • ማድሪዶች ከባየር ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ያደረጓቸውን ያለፉት አምስት ጨዋታዎችን በሙሉ ማሸነፍ ሲችል፣ በእነዚህም 13 ግቦችን አስቆጥሮ አራት ግቦች ደግሞ ተቆጥሮበታል።
  • ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከባየር ጋር ባደረጉት ያለፉት ሶስት ጨዋታዎች ላይ ሰባት ግቦችን አስቆጥሮባቸዋል። ከባየር ጋር በአጠቃላይ ካደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች ደግሞ ዘጠኝ ግቦችን አስቆጥሯል።
  • ቶኒ ክሩዝ በ2014 ወደማድሪድ ከመዛወሩ በፊት የእግርኳስ ህይወቱን ለጀመረበት ባየር ሙኒክ 200 ጨዋታዎችን አድርጓል።
  • አሪያ ሮበን በ2009 ወደጀርመን ከመዛወሩ በፊት በሜሪንጋዎቹ ሁለት የውድድር ዘመን በማሰለፍ በ2008/08 የላ ሊጋ ዋንጫን ማንሳት ችሏል።

ስለድልዱሉ የተሰጡ አስተያየቶች

የባየር ሙኒኩ አሰልጣኝ የፕ ሄንክስ፡ “እጅግ አስቸጋሪ ጨዋታ ነው። የሶስትዮሽ ዋንጫ ባለቤት በሆንበት የውድድር ዘመን [2012/13] ላይ ጥሩ ትውስታ አለኝ። ከጁቬንቱስ እና ባርሴሎና ጋር በሜዳችን ነበር የተጫወትነው። ይህ ደግሞ ጥሩ ነገር እንደሚሆን ተስፋ አለኝ።

የባየር የስፓርቲንግ ዳይሬክተር የሆኑት ሃሳን ሳሊሃሚዚክ፡ “በጣም ከባድ ጨዋታ ነው። ባለፈው ዓመት በእነሱ [ከውድድሩ] ውጪ ሆነናል። በዚህ ዓመት የተሻለ ነገር ማድረግ እንፈልጋለን። ለፍፃሜ መድረስ ከፈለግክ ሁሉንም ቡድን ማሸነፍ መቻል አለብህ። እኔም ቀናውን ነው የማስበው።”

የሪያል ማድሪድ የተቋማዊ ግንኙነት ጉዳዮች ኃላፊው ኤሚሊዮ ቡትራጉዌኖ፡ “ወደበናባው [የመልሱ ጨዋታ] ከማምራታችን በፊት በሙኒክ ጥሩ ውጤት ማግኘት ይጠበቅብናል።በውድድሩ በዚህ ደረጃ አለመቸገርህ የማይሆን ነገር ነው። ለፍፃሜው ለመብቃትም ይህን ማድረግ አለብን። እስካሁን ከፓሪስ፣ ጁቬና ባየር ጋር በመደልደል ከባድ የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታዎች ገጥሞናል።”