አጉዌሮ የሲቲ የዋንጫ ድል ያለ ድራማ በመጠናቀቁ አስደስቶታል

የማንችስተር ሲቲው አጥቂ ሰርጂዮ አጉዌሮ ሲቲ በዚህ የውድድር ዘመን ከመጨረሻው ጨዋታ በፊት ያለምንም ድራማ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት የሚችሉ መሆናቸው ረፍት ሰጥቶታል።

ማንችስተር ዩናይትድ እሁድ አመሻሹ ላይ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ በሚገኘው ዌስት ብሮምዊች አልቢዮን 1ለ0 በመሸነፉ የሲቲ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮንነት አስቀድሞ ተረጋግጧል።

በ2012-13 የውድድር ዘመን ድራማዊ በሆነ ክስተት በውድድር ዘመኑ የመጨረሻ ጨዋታ በጭማሪ ሰዓት ሲቲን ለዋንጫ ባለቤትን ያበቃችውን የማትዘነጋ ግብ ማስቆጠር የቻለው አጉዌሮ በዚህ ዓመት በፔፕ ጋርዲዮላ አስደናቂ የአጨዋወት ዘዴ ያ አይነቱ ጀግንነት አስፈላጊ አለመሆኑ እንዳስደሰተው ተናገሯል።

“ይህ ከሲቲ ጋር ሶስተኛዬ ነው። በዚህኛው ላይ የመጨረሻውን ቀን መጠበቅ አለማስፈለጉ እፎይታን የሚሰጥ ነው።” ሲል አጉዌሮ ተናግሮ “ይህ የውድድር ዘመን አስደናቂ እና ያሳየነው የአጨዋወት መንገድና የቡድን ውህደት ምርጥ ነበር።

“ከዚህ ቡድን ጋር መጫወት እና በዚህ የውድድር ዘመን ላይ ላሳካናቸው ማንኛውም ስኬቶች አካል መሆን የሚያስደስት ነው።

“በዚህ ለረጅም ጊዜያት ለቆዩት እንደዴቪድ ሲልቫ፣ ቪንሰንት ኮምፓኒ እና ያያ [ቱሬ] ላሉት ይበልጥ ልዩ ነገር ነው። ምክኒያቱም ይህ ዳግመኛ በጋራ የምናሸንፈው ሌላ የዋንጫ ክብር ነው።” ሲል ተናግሯል።

አጉዌሮን በኪውፒአር ላይ ያስቆጠራትን የጭማሪ ሰዓት ግብ ቪዲዮ ከታች ይመልከቱ።

Advertisements