‘የተቀረው ነገር አየስጨንቀኝም።” – ሻምፒዮንስ ሊጉን እየማተረ የሚገኘው ሳላህ

የሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ከፍተኛ ጉጉት ያለው የሊቨርፑሉ ኮከብ መሐመድ ሳላህ በግሉ ከሚያገኛቸው ድሎች ይልቅ ባለትልልቅ ጆሮውን ዋንጫ ማንሳት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

የ25 ዓመቱ ግብፃዊ ተጫዋች ከሮም ወደሊቨርፑል ከተዛወረ ወዲህ በአንፊልድ በነበረው የመጀመሪያ የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች ላይ በ45 ጨዋታዎች 40 ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል።

ተጫዋቹ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ “ከሻምፒዮንስ ሊጉ እና ከወርቅ ጫማው መምረጥ የሚኖርብኝ ከሆነ በእርጥም ምርጫዬ ሻምፒዮንስ ሊጉ ይሆናል። ያለምንም ጥርጥር ሻምፒዮንስ ሊጉ ነው።

“ሻምፒዮንስ ሊጉን ማንሳት ለማንም ሰው እጅግ በጣም ትልቅ ነገር ነው። የተቀረው ነገር አያስጨንቀኝም።” በማለት ተናግሯል ። ዝርዝር ዜናውን ይህን ተጭነው ያንቡ።

Advertisements