ሰርጂዮ አጉዌሮ በጉልበቱ ላይ ቀዶ ጥገና የተደረገለት መሆኑን ገለፀ

የማንችስተር ሲቲው አጥቂ ሰርጂዮ አጉዌሮ በጉልበቱ ላይ የቀዶ ጥገና ህክምና እንደተደረለትና ከዓለም ዋንጫው በፊት ወደመልካም አቋሙ ለመመለስ ያለውን ከፍ ያለ ተነሳሽነት ገልፅዋል።

የ29 ዓመቱ አርጄቲናዊ ተጫዋች ሲቲ ቼልሲን 1ለ0 መርታት ከቻለበት የካቲት ወር የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወዲህ የመጀመሪያ ተሰላፊ ሆኖ መጫወት አልቻለም።

ለመጨረሻ ጊዜ ከተቀያሪ ወንበር ላይ ተንስቶ መሰለፍ የቻለውም አጥቂው በሜዳ ላይ ከ24 ደቂቃዎች በላይ መሮጥ እንደቸገረው በገለፀበትና ከሊቨርፑል ጋር በተደረገው በሻምፒዮንስ ሊጉ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ላይ ነበር።

ይሁን እንጂ ተጫዋቹ “በጉልበቴ ላይ ከተደረገልኝ የአርትሮስኮፒ [የቀዶ ጥገና ህክምና] እያገገምኩ ነው። በቶሎ ወደሜዳ ለመመለስም ከፍተኛ የተነሳሽነት ስሜት አለኝ።” ሲል ዛሬ [ማክሰኞ] በፃፈው የግል ይፋዊ የትዊተር ገፁ ገልፅዋል።

የፕሪሚየር ሊጉ የድል ጉዞ በሲቲ አሸናፊነት በመጥናቀቁ እና የክለቡ የሻምፒዮንስ ጉዞ በሊቨርፑል በመገታቱ አጉዌሮ ወደጨዋታ እንዲመለስ የሚያስገድደው አጣዳፊ ምክኒያት የለም።

ይሁን እንጂ አጥቂው ከአይስላንድ ጋር የፊታችን ሰኔ ወር በሚደረገው የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ላይ በመሰለፍ ለአርጄንቲና ብሄራዊ ቡድን ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ይጥበቃል።

Advertisements