ቅ/ጊዮርጊስ ከካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ውጪ ሆነ

ፈረሰኞቹ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወደ ምድብ ድልድል መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት ማስመዝገብ አልቻሉም።

በካፍ ቻምፕየንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ላይ በዩጋንዳው ሻምፕዮን ኬሲሲኤ ተሸንፎ ወደ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የተቀላቀለው ቅ/ጊዮርጊስ ከኮንጎው ካራ ብራዛቪል ጋር ያደረገው የመልስ ጨዋታ በመለያ ምት ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።

በ አ/አ ስታድየም የተደረገው የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያው ጨዋታ ፈረሰኞቹ በአዳነ ግርማ ብቸኛ ጎል ማሸነፋቸው ይታወሳል።

በስታድ አልፎንሶ ማሳምባ ስታድየም የተደረገው የዛሬው አመሻሽ ጨዋታ ላይ ባለሜዳዎቹ 47ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያውን ጎል ማስቆጠር ችለዋል።

ጨዋታውም በዚሁ ውጤት በመጠናቀቁ በአጠቃላይ ውጤት ሁለቱ ቡድኖች 1-1 በመለያየታቸው በተሰጠው የመለያ ምት ካራ ብራዛቪል 4-3 በማሸነፉ ወደ ምድብ ድልድሉ ተቀላቅሏል።

በተመሳሳይ በሀዋሳ ስታድየም ወላይታ ድቻ በአጠቃላይ ውጤት በያንግ አፍሪካ 2-1 ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ መሆኑ ይታወሳል።

Advertisements