“ስለዚያ አልጨነቅም።” አርሰን ቬንገር የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን አስመልክተው የተናገሩት

አርሰን ቬንገር የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን አስመልክቶ እየተወራባቸው ስላለው ነገር እንደማይጨነቁ ገልፀው፣ ይልቁንስ የዚህ የውድድር ዘመን አቢይ ትኩረታቸው የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ማንሳት እንደሆነ ገልፀዋል።

የ68 ዓመቱ አሰልጣኝ በመድፈኞቹ ለሁለት ዓመታት የሚያቆያቸውን የኮንትራት ስምምነት የፈርሙት ባለፈው ክረምት ነበር።

ነገር ግን በቅርቡ እየወጡ ያሉ ዘገባዎች የሚያመክቱት የቀድሞው የክለቡ አምበል እና ታሪካዊ ተጫዋች ፓትሪክ ቪየራ የአሰልጠኝነቱን ሚና እንደሚረከባቸው እና መጥፎ ጊዜን እያሳለፉ የሚገኙበት ይህ የውድድር ዘመን ሲጠናቀቅ ክለቡን እንደሚለቁ ነው።

ይሁን እንጂ እየተወሩ ያሉት ጭምጭምታዎችን እስመልክተው እሁድ ከዌስት ሃም ጋር የሚያደረጉትን ጨዋታ አስታከው የቀረበላቸው መሰቀለኛ ጥያቄ ቬንገርን አላስደሰተቸውም።

ይልቁንስ አሰልጣኙ በፕሪሚየር ሊጉ በስድስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ክለባቸው “በሚገባ ገፍቶ መሄድ እንዳልቻለ።” በማመን የዩሮፓ ሊግ ሻምፒዮን በመሆን የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን የማረጋገጥ ጉዳይ እንደሚያስጨንቃቸው ተናግረዋል።

“የእኔ የግል ሁኔታ የእኔ ጭንቀት አይደለም።” ሲሉ ፈረንሳያዊው አሰልጠኝ ተናግረው። “የእኔ ጨንቀት በውድድር ዘመኑ በርካታ ውጤታማ ያልነበሩ ነገሮችን ወደስኬት መቀየር ነው። ያ ነው እኔን የሚያሳስበኝ።” ብለዋል።

እየወጡ ያሉ ዘገባዎችን መሰረት በማድረግ ክለቡን መልቀቃቸው ወይም ለተጨማሪ አንድ አመት መቆየታቸው የሚወሰነው የእርሳቸው ወይም የክለቡ ስለመሆኑ ለቀረበላቸው ጥያቄም “ያ የሚያሳስብ ነገር አይደለም።

“ያለፈውን የ[አሰልጣኝነት] የስራ ዘመኔን ወደኋላ ተመልሳችሁ ከተመለከታችሁ ሁልጊዜም ቅድሚያ እሰጠው የነበረው ለአርሰናል እግርኳስ ክለብ ነበር።

“ለውጤቶቹ ተጠያቂው እኔ ነኝ። ሰዎችም ይህን ይጠይቃሉ። በእዚህ ላይ የተካንኩ አይደለሁም። ብቸኛ የተካንኩበት ነገር
ቃል ለገባሁለትና ለስራዬ ነው።” ሲሉ መልሰዋል።

የ68 ዓመቱ አሰልጣኝ ስለወደፊት ዕጣ ፈንታቸው በግልፅ ባይናገሩም አበይ ትኩረታቸው ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር የሚያደርጉትን አስቸጋሪ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በዩሮፓ ሊጉ ስኬታማ ለመሆን እንደሆነ ገልፀዋል።።

“[የወደፊት ዕጣ ፈንታዬ] ከምንም በላይ ቅድሚያ የምሰጠው ነገር አይደለም…ቅድሚያ የምሰጠው ለዩሮፓ ሊጉ ነው።” በማለት ተናግረዋል።

“በፕሪሚየር ሊጉ ብዙም መጓዝ አይኖርብንም።

“እኛ አርሰናሎች ነን። እናም ዋንጫ ማሸነፍ እንፈልጋለን። ሁሉም ጨዋታ ደግሞ ወሳኝ ነው።

“በሜዳችን ጥሩ የውድድር ዘመን ነበርን። ያልተሳካልን ከሜዳችን ውጪ ነው።

“ለእኛ እነሱን [አትሌቲኮዎችን] ማሸነፍ እና ፍፃሜ ላይ በመድረስ ውድድሩን ማሸነፍ በጣም ወሳኝ ነገር ነው።

“በግማሽ ፍፀሜው ትልቅ መሰናክል እና ደንቃራ አለብን። እኔ ራሴ አትሌቲኮ ማድሪድ ውድድሩን የማሸነፍ የተሻለ ዕድል እንዳለው ማሳየቱን እናገራለሁ። ነገር ግን እነሱን ለማሸነፍ የተሻለንን ሁሉ እንደምናደርግ አምናለሁ።” በማለት ቬንገር ገልፀዋል።

Advertisements