ከቼልሲ ይልቅ በርንሌይን ማሰልጠን ከባድ አለመሆኑን አንቶኒዮ ኮንቴ ገለፁ

አንቶኒዮ ኮንቴ ከሺን ዳይችም ሆነ ላለመውረድ እንደሚፋለሙ ከሚጠበቁትና ዝቅተኛ የዝውውር በጀት ካላቸው አሰልጣኞችም በላይ ስራቸው ከባድ እንደሆነ ያምናሉ

የፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በአምስተኛ ደረጃ ላይ በሚገኘው ቼልሲ እና በሰባተኛ ደረጃ ላይ በሚገኘው በርንሌይ መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት ጠባብ መሆኑን ያሳያል። ነገር ግን የደረጃውን ልዩነት የምንመለከትበት የንፅፅር መነፅር ይህን ይበልጥ ያወሳስበዋል። ያለፈው ዓመት ሻምፒዮኑ ቼልሲ ከዳይቹ ባርንሌይ ጋር የዩሮፓ ሊግ ውድድርን ለመቀላቀል መፋለሙ እንደትልቅ ውድቀት ሊቆጥረም ይችላል።

ኮንቴ ሃሙስ (ዛሬ) ምሽት በተርፍ ሙር የሚገጥሙትን በርንሌይን አድንቀው ነገር ግን በሁለቱ ክለቦች መካከል ያለው የብቃት ንፅፅር ዝውውርን በቀዳሚነት ከግምት ውስጥ ያስገባ ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን ስጋትም ገልፀዋል።

“እሱ በዚህ የውድድር ዘመን ጥሩና ታላቅ ስራ እየሰራ ይገኛል።” ሲሉ ኮንቴ ስለሺን ዳይች ተናግረው። “ነገር ግን የውድድር ዘመኑን ዝቅተኛ በጀት ይዘህ ከወራጅነት የመትረፍ ዕቅድ ይዘህ መጀመር ይበልጥ ቀላል ነው። ምክኒያቱም ዳግመኛ በሊጉ ለመጫወት እንደሚሞክር ክለብ ነው የምትቆጠረው። የሆነ ነገር ለማሸነፍ በዝውውር መስኮቱ ላይ ተሳትፎ በማድረግ ስትዘጋጅ ግን ይበልጥ አስቸጋሪ ይሆንብሃል። ምክኒያቱም አሸናፊ መሆን የሚችለው ክለብ እንድ ብቻ ነው።”

“ከደረጃው ግርጌ ከሚቀመጡ ሶስት ክለቦች አንዱ ላለመሆን ነው የምትፋለመው። ክዚያም እዚህ ቦታ ላይ ላለመቀመጥ ከሚያልሙ 10 ክለቦች አንዱ ሆነህ መቀመጥ ትችላለህ። የምትፋለመውም ይህን ለማስወገድ ብቻ ነው።

“ዋንጫ ማሸነፍ ግን በእጅጉ አስቸጋሪ ነው። ምክኒያቱም ማሸነፍ የሚችለው አንድ ቡድን ብቻ ነው። የማታሸነፍ ከሆነ ደግሞ ያልተሳከ የውድድር ዘመን እንዳሳለፍክ ቀድመህ የምትናገረው አንተ ትሆናለህ። የኤፍኤ ዋንጫውን፣ የሊጉን ወይም የካራባኦ ዋንጫውን ካላሸነፍክ የውድድር ዘመኑ ያልተሳካ ዘመን ይሆንብሃል። በዚህ ምክኒያት የተነሳም ይህን አልሞ መጫወት አስቸጋሪ ነገር ነው።”

Advertisements