ማላጋ ከአምስቱ አበይት የአውሮፓ ሊግ ክለቦች የመጀመሪያው ወራጅ ክለብ ሆነ

ማላጋ በላ ሊጋው በተከታታይ 10 ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት የገጠመው መሆኑን ተከትሎ ወደዝቅተኛው የስፔን ሊግ፣ ሴጉንዳ ዲቪዥን ወርዷል።

ቦክዌሮኔሶቹ ሃሙስ ምሽት በሊቫንቴ 1ለ0 በመሸነፋቸው በአውሮፓ አበይት አምስት ሊጎች (ላ ሊጋ፣ ፕሪሚየር ሊግ፣ ቡንደስሊጋ፣ ሴሪ አ እና ሊግ 1) ውስጥ ከሚገኙ ክለቦች በዚህ የውድድር ዘመን መውረዳቸውን ያረጋገጡ የመጀመሪያው ክለብ ሆነዋል።

ኢማኑኤል ቦአቴንግ በጭማሪ ሰዓት ያስቆጠራት ግብ ሊቫንቴን ከወራጅ ቀጠናው በአንድ ደረጃ ከፍ ማድረግ ስትችል በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ከሚገኘው እና በዚህ የውድድር ዘመን 17 ነጥቦችን ብቻ መሰብሰብ ከቻለው ማላጋ ደግሞ በ17 ነጥቦች ርቆ እንዲቀመጥ ማድረግ ችሏል።

በጥር ወር አሰልጣኙን፣ ሚሼልን ያሰናበተው ማላጋ ጆሴ ጎንዛሌዝን ምትክ አድርጎ ቢቀጥርም አምስት ጨዋታዎች ከቀሩት የላ ሊጋ ውድድር ግን ከመውረድ መትረፍ አልቻለም።

Advertisements