የፕሪሚየር ሊጉ 20 እጅግ በጣም ፈጣን ተጫዋቾች

ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እጅግ በጣም የጋለ ስሜት ካላቸው የዓለማችን ምርጥ ሊጎች መካከል አንዱ ነው። ተሳታፊ ክለቦችም በፍጥነቱ በኩል የሰጠ ብቃት ያላቸው ተጫዋቾችን ይዘዋል። ነገር ግን ከሁሉም ተጫዋቾች እጅግ ፈጣን ተብለው በቀዳሚነት ሊቀመጡ የሚችሉት የትኞቹ ናቸው?

አሃዛዊ መረጃዎችን በዝርዝር በመሰብሰብ፣ በመቀመርና በመተንተን የሚታወቀው ኦፕታ ድረገፅ የሁሉንም የፕሪሚየር ሊግ ተጫዋቾች የዚህ የውድድር ዘመን ፍጥነትን መዝግቦ 20 ፈጣን ያላቸውን ተጫዋቾችን እንደሚከተለው በቅደም ተከተል አስቀምጧል። ኢትዮአዲስ ስፖርትም እንደሚከተለው አሰናድታዋለች።

20. ጆሴ ኢዝኪዌርዶ (ብራይተን) – ከፍተኛ ፍጥነት : 34.83ኪሜ/በሰዓት

ፕሪሚየር ሊጉን በዚህ የውድድር ዘመን የተቀላቀለው ብራይተን ኢዝኪዌርዶን ፍጥነት መላውን የውድድር ዘመን የፕሪሚየር ሊጉን ተከላካዮች ለማሸበር ሲጠቀምበት አሳልፏል።

ኮሎምቢያዊው የክንፍ ተጫዋች ከሲጉለስ ጀርባ በመጫወት ለክለቡ ስኬት ሁነኛ ተጫዋች ነበር።

20. አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌን (ሊቨርፑል) – ከፍተኛ ፍጥነት : 34.83ኪሜ/በሰዓት

ኦክስሌድ-ቻምበርሌን በሊቨርፑል በሚገባ መዋሃድ ችሏል። አዲስ ማግኘት በቻለው የአማካኝነት ሚናም ጉልበቱን እና ፍጥነቱን በመጡቀሙም አስደናቂ ብቃት ማሳየት ችሏል።

20. ጆርዴን ኢቤ (ቦርንማውዝ) – ከፍተኛ ፍጥነት : 34.83ኪሜ/በሰዓት

ኢቤ በሊጉ ከፍተኛ ፍጥነትን በማሳየት ኃይለኛ ተጫዋች ነው። ብዙውን ጊዜም ይህን ፍጥነቱን የተቃራኒ ቡድን ተከላካዮችን ለመረበሽ ይጥቀምበትል።

19. ሳዲዮ ማኔ (ሊቨርፑል) – ከፍተኛ ፍጥነት : 34.84ኪሜ/በሰዓት

ማኔ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከታዩ እጅግ ፈጣን እና አደገኛ ከሆኑ የፊት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው።

ተጫዋቹ በዚህ የውድድር ዘመንም በሊቨርፑል ቡድን ውስጥ ያሳየው ብቃት ከቀደመው ጊዜ የተለየ አልነበረም።

18. መሐመድ ሳላህ (ሊቨርፑል) – ከፍተኛ ፍጥነት : 34.93ኪሜ/በሰዓት

ሳላህ በዚህ የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ እስካሁን 30 ኳሶችን ከመረብ ጋር በማዋሃድ ምርጥነቱን ማሳየት የቻለ ተጫዋች ነው።

ሳላህ ድንገት የሚያደረገው ሽምጥ ሩጫ ከአስደናቂ አጨራረሱ ጋር ተዋህዶ አደገኛ ተጫዋች እንዲሆን አድርጎታል። የሚያስደንቀው ብቸኛ ነገር ቢኖር ከም በሚያሳየው ፍጥነት ከአንድ እስከአስር ባለው ደረጃ ውስጥ መግባት አለመቻሉ ነው።

16. ጆሹዋ ኪንግ (ቦርንማውዝ) – ከፍተኛ ፍጥነት: 34.94ኪሜ/በሰዓት

ለቦርንማውዝ የፊት መስመር ፈጣን መሆን ሚስጥሩ ባለፈው ዓመትም እስከ20 ባለው ደረጃ ውስጥ መግባት ችሎ የነበረው ኪንግ ነው።

በዚህ የውድድር ዘመንም በድጋሚ ፍጥነቱን የተቃራኒ ቡድን ተከላካዮችን ለማሸበር ተጠቅሞበታል።

16. ከርት ዙማ (ስቶክ) – ከፍተኛ ፍጥነት : 34.94ኪሜ/በሰዓት

ዙማ ከከንፍ፣ ከአጥቂና ከመስመር ተከላከዮች ተርታ እዚህ ዝርዝር ውስጥ መካተቱ አስገራሚ ነው።

ኃይለኛ ፍጥነቱ የሚታየውም የተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾችን ጥቃት በፍጥነት ለመከላከል በሚያደርገው ድንገተኛ የመከላከል እንቅስቃሴ ላይ ነበር።

15. ራሂም ስተርሊንግ (ማንችስተር ሲቲ) – ከፍተኛ ፍጥነት : 34.97ኪሜ/በሰዓት

ስተርሊግን የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮንነታቸውን የውድድር ዘመኑ ሳይጠናቀቅ በፊት ያረጋገጡት ድንቅ የሲቲዎች የቡድን አካል ነው።

ተጫዋቹ በዚህ የውድድር ዘመን ከተለመደው ፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴው በተጨማሪ እስካሁን በሊጉ 17 ግቦችን ማስቆጠርም ችሏል።

13. ፒየር-ኤመሪክ አውባምያንግ (አርሰናል) – ከፍተኛ ፍጥነት : 34.99ኪሜ/በሰዓት

ኦውባምይንግ ከዶርትሙንድ አርሰናልን የተቀላቅለው በጥር ወር ቢሆንም፣ ነገር ግን ከወዲሁ ፈጣን ተጫዋችነቱን ማሳየት ችሏል።

ተከላካዮችም በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በልዩ ትኩረት ሊመለከቱት የሚገባ አጥቂ እንደሆነም ግልፅ ነው።

13. ሄክቶር ቤለሪን (አርሰናል) – ከፍተኛ ፍጥነት : 34.99ኪሜ/በሰዓት

ቤለሪን ፈጣን ተጫዋችነቱን በሊጉ ላይ ደጋግሞ ማሳየት የቻለ ተጫዋች ነው።

የአርሰናልን ፈጣን የማጥቃት ሚና ከመሰመር ተከላካይ ስፍራ ላይ ተተኩሶ እንዲነሳ በማድረግ የሚታወቅ ተጫዋችም ነው።

12. ደአንድሬ የድሊን (ኒውካሰል) – ከፍተኛ ፍጥነት : 35.08ኪሜ/በሰዓት

የልዲን በማጥቃቱ እንስቃሴ ላይ አብዝቶ መሳተፍ የሚወድ ሌላኛው ፈጣን የመስመር ተከላካይ ነው።

የተጫዋቹ ፍጥነት ኒውካሰል በመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊጉ የውድድር ዘመኑ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አድርጎታል።

11. ጄሚ ቫርዲ (ሌስተር) – ከፍተኛ ፍጥነት : 35.09ኪሜ/በሰዓት

ቫርዲ ከሊጉ እጅግ ፈጠን አጥቂዎች መካከል አንዱ ሲሆን፣ ሁልጊዜም ከተከላካዮ ጀርባ መሮጥም ምርጫው ነው።

በዚህ የውድድር ዘመንም ሌስተርን ግብ በማስቆጠር እገዛው በከፍተኛ 10 ግብ አስቆጣሪነት ተርታ ላይ መሰለፍ አስችሎታል።

10. ሎረን ኮሺየልኒ (አርሰናል) – ከፍተኛ ፍጥነት : 35.11ኪሜ/በሰዓት

ኮሺየልኒ ከሊጉ እጅግ ፈጣን የመኃል ተከላካዮች መካከል አንዱ ነው። ባለፉት ዓመታት ላይም በአርሰናል ወጥ ብቃቱን ሲያሳይ ቆይቷል።

9. ኪኮ ፌሜኒያ (ዋትፎርድ) – ከፍተኛ ፍጥነት: 35.12ኪሜ/በሰዓት

ፌሜኒያም በፍጥነት ወደፊት በመሮጥ የማጥቃቱን ሚና የሚቀላቀል ሌላው የመስመር ተከላካይ ነው።

ዋትፎርድን ባለፈው ክረምት የተቀላቀለ ቢሆንም፣ በመጀመሪያው የውድድር ዘመኑ ግን አስደማሚ ብቃት ማሳየት ችሏል።

8. ኦሊቨር ቡርኬ (ዌስት ብሮም) – ከፍተኛ ፍጥነት : 35.13ኪሜ/በሰዓት

ወጣቱ የክንፍ ተጫዋች በዌስት ብሮም ቀላል የማይባል ጊዜ ያሳለፈ ቢሆንም፣ ነገር ግን ይህ ከፍተኛ ፍጥነት ከማሳየት ሊያግደው አልቻለም።

አሃዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነም ለተጫዋቹ ገና ተጨማሪ የመጫወቻ ዕድሎችን መስጠቱ ፋይዳ ያለው መሆኑን ነው።

7. ዊልፍሬድ ዛሃ (ክሪስታል ፓላስ) – ከፍተኛ ፍጥነት : 35.14ኪሜ፡/በሰዓት

ዊልፍሬድ ዛሃ በአስቸጋሪ ጉዞ ላይ በሚገኘው ፓላስ ክለብ ውስጥ አንፀባሪቂ ብቃቱን ማሳየት የቻለ ተጫዋች ነው።

ንስሮቹ የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ውስጥ ሲገቡ የተጫዋቹ ፍጥነትና ክህሎት በእጅጉ ወሳኝ ይሆናል።

6. አንቶኒዮ ሩዲገር (ቼልሲ) – ከፍተኛ ፍጥነት: 35.19ኪሜ/በሰዓት

በዚህ ዝርዝር ውስጥ ሩዲገር መካተቱ አስገራሚ ቢመስልም በመልሶ ማጥቃት ላይ ያለው ፍጥነት ግን ለቼልሲ ያለው ፋይዳ በጅጉ ከፍ ያለ ነበር።

5. ካይሌ ዎከር (ማንችስተር ሲቲ) – ከፍተኛ ፍጥነት : 35.21ኪሜ/በሰዓት

ዎከር በዚህ የውድድር ዘመን እጅግ አደገኛ የነበረው የማንችስተር ሲቲ ፈጣን እንቅስቃሴ አካል ነበር።

ከመስመር ተከላካይነት ተነስቶ የሚያደረገው ወጥ የሆነ ሽምጥ ግልቢያ ከመነሻውም ፈጣን በሆነው የአጥቂ ክፍል ላይ ተጨማሪ ኃይል ነበር።

4.ቲዮ ዋልኮት (ኤቨርተን) – ከፍተኛ ፍጥነት : 35.23ኪሜ/በሰዓት

ዋልኮት እጅግ ፈጣን ተጫዋች መሆኑ ምንም ሚስጥር የለውም።

በዚህ የውድድር ዘመን የተለየ ነገሩ በክንፍ በኩል ይገሰግስ የነበረው ለአርሰናል ሳይሆን ለኤቨርተን መሆኑ ብቻ ነው።

3. ሞሳ ሲሶኮ (ቶተንሃም) – ከፍተኛ ፍጥነት : 35.33ኪሜ/በሰዓት

ሲሶኮ በስፐርስ ቡድን ውስጥ የተጋነነ ብቃት ያለው ተጫዋች ተደርጎ መቆጠሩ የተዘነጋ ተጫዋች አላደረገውም ማለት ሚዛናዊ አለመሆን ነው።

ነገር ግን ተጫዋቹ መጫወት በቻለባቸው ጨዋታዎች ላይ ማሳየት የቻለውን አጠቃላይ ተነሳሽነትና ብቃት ቸል ማለት ግን ይቸግራል። በተለይም ግን ፍጥነቱን መዘንጋት የማይታሰብ ነገር ነው።

2. ፓትሪክ ቫን አንሆልት (ክሪስታል ፓላስ) – ከፍተኛ ፍጥነት: 35.42ኪሜ/በሰዓት

ቫን ሆልት ከፕሪሚየር ሊጉ ፈጣን የመስመር ተከላካዮች ሁሉ በቀዳሚነት የሚቀመጥ ተጫዋች ነው።

ተጫዋቹ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወደፊት በመሄድ የሚጫወት ተጫዋችም ነው። ብዙውን ጊዜም ግብ በማስቆጠር ሚና ላይ ተሳታፊ ይሆናል።

1. ሊሮይ ሳኔ (ማንችስተር ሲቲ) – ከፍተኛ ፍጥነት : 35.48 ኪሜ/በሰዓት

ሳኔ ከፕሪሚየር ሊጉ ተጫዋቾች ሁሉ ፈጣን ተጫዋች በመሆን የቀዳሚነቱን አክሊል መድፋት ችሏል።

ለማንችስተር ሲቲ የውድድር ዘመኑ ስኬታማነትም ቁልፍ ሚና መጫወት የቻለ ተጫዋች ነው።

Advertisements