ዌንገር ከአርሰናል በአመቱ መጨረሻ እንደሚለቁ ካሳወቁ በኋላ ምን ተባለ?

 

አርሴን ዌንገር ትናንት በአመቱ መጨረሻ ላይ 22 አመት ከቆዩበት የመድፈኞቹ አሰልጣኝነት እንደሚለቁ ካሳወቁ በኋላ የቀድሞ እና አሁን ያሉት ተጫዋቾች፣አትሌቶችን ጨምሮ በስፋት አስተያየት ሰጥተዋል።በቀጣዩ መረጃ ም የተመረጡ አስተያየቶች ተሰብስበው ቀርበዋል።

ዌንገር በመግለጫቸው “በጥንቃቄ ካሰብኩበት እና ከክለቡ ጋር ከተወያየው በኋላ በአመቱ መጨረሻ ስራዬን የማቆምበት ትክክለኛ ሰአት ላይ እገኛለው። የማይረሱ ጊዜያትን ለረጅም ጊዜ ከክለቡ ጋር በማሳለፌ ኩራት ይሰማኛል።ክለቡንም በቆራጠኝነት መምራት ችያለው።” በማለት ከአርሰናል ጋር እንደሚለቁ በማሳወቅ ብዙዎች አስተያየት እንዲሰጡ የተገደዱበትን ውሳኔ አሳልፈዋል።

አስተያየት ከሰጡት ውስጥ አሰልጣኞች ፣ተጫዋቾች እና አትሌቶች ይገኙበታል።

ፓትሪክ ቪየራ

“ለሁሉም ነገር አመሰግናለው።”

አሮን ራምሴ

“ላንተ በመጫወቴ እንዲሁም ካንተ ጋር ዋንጫ በማሸነፌ ኩራት ይሰማኛል።አንተ በህይወቴ ከልጅነቴ ጀምሮ ትልቅ እስክሆን ድረስ በሜዳ ላይና ከሜዳ ውጪ ትልቅ ተፅእኖ ፈጥረሀል።ዛሬ ሁሉም ሰው የክብር መልእት እየፃፉ ሲያሳዩ በመመልከቴ ደስተኛ ነኝ።ምክንያቱም ከዚህ በላይ ይገባሀል።አመሰግናለው።”

ፒየር ኤምሪክ አውባሚያንግ

“እኔ ያንተ የመጨረሻ ፈራሚ ነኝ፣ነገርግን እዚህ ከመጣው ጀምሮ ያንተ ተጫዋች በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል።ለሁሉ ነገር አመሰግናለው።”

አሽሊ ኮል

“በኔ ላይ እምነት አድሮበት በትልቅ ቡድን እንድጫወት ላደረገኝ አሰልጣኝ ለሁሉም ነገር አመሰግናለው።በኔ ላይ እምነት እንዳለህ የነገርከኝ ውይይታችን አልረሳውም።ለነበረን መልካም ትዝታ አመሰግናለው በቀጣዩ መልካም ነገር ይግጠምህ።”

ፒተር ቼክ

“ዛሬ ከተሰማው ትልቅ ዜና በኋላ ሁሉም መድፈኞች በክለቡ ትልቅ ነገር እና ታሪክ ለሰሩት ዌንገር ያላቸውን ፍቅር እና ክብር የሚገልፁበት አጋጣሚ አግኝተዋል።ከክለቡም ሲለቁም ሌላ ዋንጫ አግኝተው እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለው።ይህን ለማድረግ ደግሞ የኛ ሀላፊነት ነው።”

ኢዎቢ

“ለአርሰናል ክለብ ላደረከው ሁሉ ነገር በእኔም ላይ በልጅነቴ እምነት ስላደረብህ፣እራሴን እንደ ሰው እና እንደ ተጫዋች እንዳድግ እድሉን ስለሰጠኸኝ ሁልጊዜም አመሰግንሀለው።በጣም አመሰግንሀለው።እወድሀለው። ❤

ሶል ካምቤል

“ዋው!”

ዴቪድ ሲማን

“የዌንገር መልቀቅ ዜና ለአርሰናል መጥፎ እለት ነው።አሁን የሚገባውን ክብር ልንሰጠው እንችላለን?”

ሞ ፋራህ

“ለአርሰናል ለሰራኸው እና ለነበረው ትዝታ ምስጋና ይገባሀል።መሄድህን ሳይ ሀዘን ተሰምቶኛል።”

አርሰናል

ጀግና!

Advertisements