ማንችስተር ዬናይትዶች የጄሲ ሊንጋርድን ሳምንታዊይ ደሞዝ ከፍ ሊያደርጉለት ነው።

Image result for lingard

ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

የማንችስተር ዬናይትድ አካዳሚ ውጤት ለሆነው እንግሊዛዊዬ የፊት መስመር ተጨዋች ጄሲ ሊንጋርድ በሳምንት 100 ሺ ፖውንድ ተከፋይ ሊያደርጉት እንደሆነ ዲይሊ ስታር ዘግቧል.

የ25 አመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ሊንጋርድ በዚህ የውድድር ዘመን በቀያይ ሰይጣኖች ቤት ከምንግዜውም በላይ ምርጥ አቋምን እያሳየ የሚገኝ ሲሆን ላሳየው ምርጥ ብቃትም ተገቢውን ክፍያ ሊሰጡት ነው።

ጄሲ ሊንጋርድ በቀያዬቹ ሰይጣኖች ቤት በዚህ የውድድር ዘመን ከአጥቂው ሮሚሉ ሉካኩ ቀጥሎ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን በሁለተኛነት ደረጃ ላይ መቀመጥ ሲችል ሊንጋርድ በዬናይትድ ቤት የሚያቆየውን የ4 አመት ኮንትራት ከፈረመ 12 ወራትን ሆኖታል።

ሊንጋርድ ገና በጩጬነቱ በአባቱ አማካኝነት በሊቨርፑሎች አካዳሚ ለሙከራ የሄደ ቢሆንም ማለፍ ሳይችል ቀርቶ ወደ ዬናይትድ አካዳሚ በማምራት ዬናይትድን መቀላቀል ችሏል፤ ጄሲ ሊንጋርድ የዬናይትድን ባህል በጣም ከሚያውቁ ወጣት ተጨዋቾች በግንባር ቀደምነት የሚጠራ ተጨዋች ነው።

Advertisements