የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ተደረገ

በሳምንቱ አጋማሽ በተደረጉ ጨዋታዎች አላፊ ቡድኖች ከተለዩ በኋላ የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሲደረግ ሶስት የምስራቅ አፍሪካ ቡድኖች በአንድ ምድብ ተገናኝተዋል።

ምስራቅ አፍሪካ ከሌላ ጊዜ በተለየ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ብዛት ያላቸውን ክለቦች ማሳተፍ ችላለች።

እነሱም የታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ፣የሱዳኑ አል ሂላል፣የሩዋንዳው ራዮን እና የኬኒያው ጎርማሂያ ናቸው።

ወደ ምድብ ድልድሉ መቀላቀል የቻሉ 16 ቡድኖች ባለፉት 5 አመታት ያላቸውን ውጤታማነት ግንዛቤ ውስጥ ተካቶ በተዘጋጀላቸው ቋት መሰረት ተደልድለዋል።

በዚህም መሰረት ዩኤስ ኤም አልጀርስ፣ኢንየምባ፣አልሂላል እና ኤ ኤስ ቪታ የምድብ አባት በመሆን የእጣ ድልድሉ ይፋ ሆኗል።

በድልድሉም ከምስራቅ አፍሪካ ተወካዮች ውስጥ ሶስቱ በአንድ ምድብ ውስጥ መካተት ችለዋል።

በምድብ አራት ዩ ኤስ ኤም አልጀርስ፣ጎርማሂያ፣ራዮን እና ያንግ አፍሪካ የተደለደሉ ሲሆን ይህም የምስራቅ አፍሪካ ክለቦች ፍልሚያ የሚታይበት ይሆናል።

ሙሉ ድልድል

ምድብ አንድ: ራጃ ካዛብላንካ፣አሴክ ሚሞሳክ፣አዱና ስታርስ፣ኤኤስ ቪታ 

ምድብ ሁለት: አል ማስሪ፣ዩዲ ሶንጎ፣አር ኤስ ብርካኔ፣አልሂላል

ምድብ ሶስት: ጆሊባ፣ዊሊያምስቪል፣ካራ ብራዛቪል፣ኢኒይምባ

ምድብ አራት: ራዮን ስፖርት, ጎርማሂያ፣ያንግ አፍሪካ፣ዩ ኤስ ኤም አልጀርስ