ሞሀመድ ሳላህ የ2017/18 የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን ተሸለመ።

Image result for mohamed salah pfa

የቀያዬቹ ኮከብ ሙሀመድ ሳላህ የማንችስተር ሲቲውን ኬበን ዴቡረነ እንዲሁም ሀሪኬንን በመብለጥ የ2017/18 የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን ማሸነፍ ችሏል።

የአንፊልዱ የፊት መስመር ተጨዋች በዚህ የውድድር ዘመን ባሳየው አስገራሚ አቋም ምክንያት በፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር አባላት በመመረጥ በ92 የፕሪሚየር ሊግ እና የእግር ኳስ ሊግ አባላት በተገኙበት እሁድ ምሽት ለንደን ላይ ሽልማቱን ተቀብሏል።

ሙሀመድ ሳላህ በቀዬቹ ቤት በዚህ የውድድር ዘመን በ 46 ጨዋታዋች 41 ጎሎችን በማስቆጠር አስገራሚ የጨዋታ ዘመንን እያሳለፈ የሚገኝ ሲሆን ይህ አቋሙም በተፎካካሪነት ከቀራቡት ከዴኬበን ዴቡረነ, ሀሪኬን , ዴቪድ ዴህያ , ዴቪድ ሲልቫ እንዲሁም ሌሮይ ሳኔን በማሸነፍ ኮከብ ተጨዋች መሆን ችሏል።

ግብፃዊዬ ሙሀመድ ሳላህ እስከዛሬ በሊቨርፑል ተጨዋቾች ይህንን ሽልማት ከተቀበሉት ስምንተኛው ተጫዋች ሲሆን ሊውስ ሰዋሬዝ ፤ ስቴቨን ጀራርድ ፤ ኢያን ራሽ ፤ ጆን ቤርነስ ፤ ኬኒ ዳግሊሺ እንዲሁም ቴሪ ማክዴርሞት መሸለም ችለዋል። ሳላህም በመሸለሜ ደስተኛ ነኝ አሁንም ጠንክሬ ሰራለው ቅድሚያ ለቡድኔ እንጂ ለእራሴ አስቤ አላውቅም ከዚህ በላይ ክቡድኑ ጋር የማነሳው ለእኔ ትልቅ ቦታ አለው ሲል ተናግሯል።

Advertisements