ኤልኒኒ የቁርጭምጭምቲ ጉዳት እንደገጠመው ክለቡ በይፋ ገለፀ

አርሰናል ተጫዋቹ ሞሐመድ ኤልኒኒ ምንም እንኳ እሁድ ዕለት የቁርጭምጭሚት ጉዳት እንደደረሰበት ቢገልፅም፣ ይህ የውድድር ዘመን ከመጠናቀቁ በፊት በፊት ግን ተጫዋቹ ወደሜዳ እንደሚመለስ ተስፋ አድርጓል።

ግብፃዊው ተጫዋች መድፈኞቹ በኤመራትስ ስታዲየም ዌስትሃምን 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ በቻሉበት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በማርክ ኖብል ተገጭቶ በደረሰበት ጉዳት በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በቃሬዛ ታግዞ ከሜዳ ለመውጣት ተግዷል።

በዚህ ጉዳት የተነሳም ተጫዋቹ ግብፅ ከ18 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በምትሳተፍበት የፊታችን ሰኔ ወር ለሚደረገው የዓለም ዋንጫ የመጫወት ተስፋው እንዲደበዝዝ ሆኖ ነበር።

ይሁን እንጂ መድፈኞቹ የ25 ዓመቱ አመካኝ እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ከሜዳ ተገልሎ ይቆያል የሚለውን ግምት ወደጎን በማለት አርሰናል ግንቦት ወር ላይ ለሚደረገው በዩሮፓ ሊጉ ፍፃሜ የሚያልፍ ከሆነ ተጫዋቹ በጨዋታው ላይ የመሰለፍ ዕድል እንደሚኖረው ገልፀዋል።

“ሞ በዚህ የውድድር ዘመን ለአርሰናል ዳግመኛ እንደሚስለፍ ተስፋ አያደረግን ነው። ከግብፅ እግርኳስ ማህበር ጋር መደበኛ ግንኙነት ማድረጋችንንም እየቀጠልን ነው።” ሲል ክለቡ በመግለጫው ገልፅዋል።

ኤልኒኒ በዚህ የውድድር ዘመን ለሰሜን ለንደኑ ክለብ 13 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል።

Advertisements