የቡፎን ድርጊት ሊረዱት የሚችሉት ተግባር እንደሆነ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ገለፁ

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አሌክሰንደር ሴፌሪን ጂያንሊጁ ቡፎንን በሻምፒዮንስ ሊጉ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ጁቬንቱስ በሪያል ማድሪድ በተሸነፈበት ጨዋታ በዳኛው ማይክል ኦሊቨር ላይ በፈፀመው ድርጊት ሊወቀስ ከሚገባ ይልቅ ድርጊቱን “ሊረዱት የሚችሉት’ ተግባር እንደሆነ ገልፀዋል

ጁቬ በሻምፒዮንስ ሊጉ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በመጀመሪያው ጨዋታ በቱሪን የተቆጠረበትን የግብ ብዛት ያህል በሳንቲያጎ በርናቢየው እስከጭማሪ ሰዓት 3ለ0 በመምራት ጨዋታውን ለማጠናቀቅ ከጫፍ መድረስ ችሎ ነበር።

ይሁን እንጂ እንግሊዛዊው ዳኛ ኦሊቨር መድሂ ቤናሺያ በጨዋታው መጠናቀቂያ ሰዓት በሉካስ ቫስኬዝ ላይ ፈፅሞታል ባሉት ጥፋት ማድሪድ የፍፁም ቅጣት ምት ማግኘት ችሏል። በዚህ ውሳኔ ደስተኛ ያልነበረው ቡፎን ባሳየው የብስጭት ድርጊትም ለቀይ ካርድ ተዳርጓል።

ቡፎን ለጨዋታ በኋላ የኦሊቨርን ውሳኔ ተቃውሞ የዳኛውን ድርጊት “ቆሻሻ” እና ዳኛው እንዲህ ዓይነቱን ጨዋታ የመዳኘት ልብ የሌላቸው እንደሆነ ገልፃ ነበር።

በዚህም ምንም እንኳ ኦሊቨር እና ባለቤታቸው በርካታ የማስፈራሪያ ዛቻ የደርሰባቸው ቢሆንም ሴሬፊን ግን የቡፎን ድርጊት ይቅር የሚባል እንደሆነ ገልፀዋል።

“እሱ [ቡፎን] ያደረገው ነገር መጠን ያለፈ ቢሆንም፣ ነገር ግን ሻምፒዬንስ ሊጉን ማሸነፍ የሚችልበት የመጨረሻ ዕድሉ በመሆኑ ድርጊቱን በሚገባ ተረድቼለታለሁ።” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ለስፔኑ ጋዜጣ ማርካ ተናረዋል።

“እሱ ሰብዓዊ ፍጡር ነው። እናም ልረዳው ይገባል። እኔም በበጎ ምግባር በመጨረሻው የቅዳሜ ጨዋታ ከጓደኞቼ ጋር ኳስ በምጫወትበት ወቅት እና በመጨረሻው ሰዓት ሽንፈት ሲገጥመኝ የቀድሞ ተጫዋቾዥ ከዳኛው ጋር ተደባድበው ነበር።

“[እግር ኳስ] ስትጫወት እና ወደሜዳ ስትገባ ማሸነፍ ትፈልጋለህ። ስለሁሉም ነገርም ትናገራለህ። ስለሁሉም ነገርም አስተያየትህንም ትሰጣለህ። በስሎቫኒያ በምጫወትበት ወቅትም ይኸው ነገር በእኔም ላይ ሆኖ ነበር።

“ግማሹ የዓለም ህዝብ ፍፁም ቅጣት ምት እንደነበር ያስባል። የተቀረው የግማሹ ሃሳብ ደግሞ እንዳልሆነ ነው። ዳኛው ደግሞ የፍፁም ቅጣት ምት ነው ብለው ወስነዋል። እግርኳስ ደግሞ እንዲህ ነው።

“ይህ የጁቬ ብስጭት ይገባኛል። ምክኒያቱም ከውድድሩ የወጡት በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ነበር። ነገር ግን የሪያል ማድሪድ ተጫዋቾችም ኦሊቨር ወደተጨማሪ ሰዓት ወይም ወደፍፁም ቅጣት ምት የሚያመራ ፊሽካ እንዳይነፉ ሲሉ ያሳዩትንም ብስጭት አርዳለሁ።

“ይህ እግርኳስ ነው። ይህ ስፖርት ነው። ይህ ህይወት ነው። በመጨረሻው ሰአት መሸነፍ ደግሞ በእጅጉ ከባድ ነው።”

Advertisements