የአርሰናል የ2018/19 የውድድር ዘመን አዲስ መለያ አፈትልኮ ወጣ

የድህረ አርሰን ቬንገር ዘመን የአርሰናል የመጀመሪያ መለያ ይፋዊ ባልሆነ መንገድ አፈትልኮ ወጥቷል።

ነገር ግን በስፖርት ትጥቅ አምራቹ ፑሜ የሚመረተው የመጨረሻው የክለቡ መለያ ሊሆን እንደሚችልና አዲዳስ ወይም ናይክ ቀጣዩ የክለቡ የትጥቅ አምራች እንደሚሆኑም ይጠበቃል።

ይፋዊ ባልሆነ መንገድ አፈትልኮ የወጣው የመድፈኞቹ መለያ የተለመደው ነጭ እጀታ ያለው ቀይ መለያ እንዳለ ቢሆንም በሁለቱም በኩል ግን ግብ ቀይ ባለመስመር ክፈፎች አሉት።

ይሁን እንጂ የክለቦች መለያ በይፋ ለህዝብ ከመተዋወቁ በፊት አፈትልከው የሚወጡ መለያዎችን ይፋ በማድረግ የሚታወቀው ፉቲ ሄድላየንስ ድረገፅ ይፋ ያደረገው የአርሰናል አዲሱ መለያ ክለቡ በዚህ የውድድር ዘመን ከተጠቀመው ቀለም ጠቆር ያለ ቀይ ቀለም አለው።

አፈትልኮ የወጣው የአርሰናል የ2018/19 የውድድር ዘመን አዲስ መለያ

የአርሰናል ቁምጠና ካልሲም እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ሙሉ በሙሉ ነጭ ነው።

የ2018/19 አዲሱ የአርሰናል መለያ በመጪው ሰኔ ወር በክለቡ በይፋ እንደሚተዋወቅ ይጠበቃል።

አርሰናሎች በሜዳቸው ውጪ ለብሰው የሚጫወቱት ሁለተኛ መለያ በኢንተርኔት ይፋዊ ባልሆነ መልኩ የተለቀቀው በቀድሙት ወራት ነበር። ይሁን እንጂ ብዙዎች የመለያውን ንድፍ የወደዱት አይመስለም።

አፈትልኮ የወጣው የአርሰናል የ2018/19 የውድድር ዘመን ሁለተኛ መለያ

መድፈኞቹ በአሁኑ ጊዜ ከትጥቅ አምራቹ ፑሜ ጋር በዓመት 30 ሚ.ፓውንድ ክፍያ ያስሩት ውል በሚቀጥለው የውድድር ዘመን መጨረሻ ይጠናቀቃል።

እናም የሰሜን ለንደኑ ክለብ ከፕሪሚየር ሊጉ ተቀናቃኝ ክለቦች በታች የሚያደረገውን ይህን ስምምነት ከፍ ለማድረግ ፍላጎት ያላቸው በመሆኑ ከሁለቱ ዝናኛ የትጥቅ አምራቾች አዲዳስ እና ናይክ ጋር ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ።

አርሰናል መለያውን በ2014-15 የውድድር ዘመን ለብሶ ለመጫወት ከፑሜ ጋር ይፋዊ ስምምናት ያደረገው በ2013 ነበር።

ነገር ግን ስምምነቱ ማንችስተር ዩናይትድ ከአዲዳስ ጋር ከተዋዋለው 75 ሚ.ፓውንድ ዓመታዊ ክፍያ እና ቼልሲ ከናይክ ጋር ከተዋዋለው 60 ሚ.ፓውንድ ክፍያ ጋር ሲነፃፅር እዚህ ግባ የማይባል ነው።

Advertisements