ሞ ሳላህ የባላንዶር አሸናፊ ለመሆን ጥሩ እድል እንዳለው ኢያን ራይት ገለፀ

የቀድሞ የአርሰናል አጥቂ የነበረው ኢያን ራይት ሞ ሳላህ በፕሪምየርሊጉ እና በቻምፕየንስ ሊጉ ላይ እያሳየ የሚገኘው አስደናቂ አቋም የባሎንዶር አሸናፊ ለመሆን ጥሩ እድል እንዳለው አሳወቀ።

ግብፃዊው የምርጥ የግራ እግር ባለቤት ትናንት ምሽት በአንፊልድ ሊቨርፑል ሮማን 5-2 ሲያሸንፉ የተለመደውን ድንቅ ብቃቱን ማሳየት ችሏል።

በጨዋታው ሁለት ያማሩ ድንቅ ጎሎችን ሲያስቆጥር ለሌሎቹ ሁለት ጎሎች መገኘት ደግሞ አመቻችቶ በማቀበል ጉልህ ሚና ተጫውቷል።

ተጫዋቹ በተለይ ያስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ጥራት እና ውበት በእርግጥም ዘንድሮ የተለየ አመት ላይ እንደሚገኝ ያሳየ ነበር።

ከሁለቱ ጎሎች በኋላ ለቀድሞ ክለቡ ሮማ ክብር ሲል ደስታውን ከመግለፅ የተቆጠበው ሳላህ ከሜሲ እና ሮናልዶ ጋር እየተነፃፀረ ይገኛል።

በርግጥም ተጫዋቹ በመጀመሪያ አመቱ ለክለቡ እየሰራ ያለው አመቱን በዋንጫ ስለማጠናቀቁ ባይታወቅም በግሉ ግን የተዋጣለት አቋም እያሳየ ይገኛል።

ተጫዋቹ ከሜሲ እና ሮናልዶ ጋር ተፎካክሮ የባሎንዶር አሸናፊ መሆን የሚያስችለው አቋም ላይ  እንደሚገኝ ብዙዎች ሀሳባቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

የቀድሞው የአርሰናል አጥቂ ኢያን ራይትም ከነዚሁ የሚመደብ ሲሆን “ሳላህ ባላንዶርን የማሸነፍ ጥሩ እድል አለው።” ሲልም ሀሳቡን ገልፇል።

ኢያን ራይት በቀጣዩ ሊቨርፑል በቻምፕየንስ ሊጉ ያለው የዋንጫ አሸናፊነት ሁኔታ እንዲሁም ሳላህ በአለም ዋንጫ ከግብፅ ጋር የሚኖረው ቆይታም የባሎንዶር አሸናፊ ለመሆን የሚኖረው እድል የሚወስን መሆኑን አስታውሷል።

የሳላህ የዘንድሮ አቋም ከሜሲ እና ከሮናልዶ አቋም ጋር መነፃፀር ይችላል? ሀሳባችሁን በኮሜንት ሳጥን ውስጥ ስጡን።

Advertisements