“በማንችስተር ዩናይትድ ማሊያ ያሳለፍኩት ምርጡ አመት ዘንድሮ ነው” – ዴሂያ

ከቀያይ ሰይጣኖቹ ጋር ለሰባተኛ አመት እየተጫወተ የሚገኘው ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሂያ የዘንድሮ አቋሙ ከሌሎቹ አመታት ሁሉ ምርጡ እንደሆነ ገለፀ።

የማን ሲቲ አስደናቂ አቋም ዩናይትዶች በሰፊ ነጥብ ከኋላ ለመከተል ቢገደዱም ለቡድኑ አሁን ለተገኘበት ቦታ በቅድሚያ ስሙ የሚነሳው ዴቪድ ዴሄያ ነው።

ባለፉት ረጅም አመታት ጀምሮ የተዋጣ ግብጠባቂ በማግኘት የሚሳካላቸው ዩናይትዶች ከቫንደርሳር በኋላ ምርጡን ዴሂያን አግኝተዋል።

ግብጠባቂው ለጎል የቀረቡ ኳሶችን በማዳን የተለየ ችሎታ እንዳለው በተደጋጋሚ በማስመስከር የፕሪምየርሊጉ እና የአለማችን አንዱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ለመሆን ችሏል።

ከወዲሁም ዘንድሮ በ 21 ጨዋታዎች ላይ[17 ቱ በፕሪምየርሊግ] ጎሉን ያላስደፈረ ሲሆን ይህም ከማን ሲቲም ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ካለው ተመሳሳይ ሪከርድ በሁለት ከፍ እንዲል ያደርገዋል።

ዴሂያ ዘንድሮ እያሳለፈው የሚገኘው አመት ለሱ ምርጡ እንደሆነ ተጠይቆ “አዎ ባለኝ አቋም በጣም ደስተኛ ነኝ።የተሟላ አቋም እንደነበረኝ አስባለው።አመቱን ሙሉ ከጉዳት ነፃ የሆነ ጥሩ ስሜት ላይ ስለበርኩ ለኔ የተለየ አመት ነበር።” በማለት ተናግሯል። 

ግብጠባቂው ለዚህ አቋሙ ለአሰልጣኙ ሞሪንሆ ቡድኑን የማነሳሳት አቅም አስተዋፅኦ እንዳደረገለት ጨምሮ አስታውሷል

“ጥሩ አሰልጣኝ አለን።ሁሉንም ያሸነፈ በጣምም ልምድ ያለው አሰልጣኝ አለን።ጥሩው ነገር ምንድነው ያለው የማሸነፍ ተነሳሽነት ወደ ሌሎቹ ተጫዋቾች ማስተላለፍ መቻሉ ነው።

“ነገርግን በመጨረሻ ሜዳ ላይ የምንገባው እኛ ነን።ሜዳ ላይ ተጫውተን፣ጥሩ እድል ፈጥረን ጎል የማስቆጠር ሀላፊነት ያለብን እኛው ነን።

“ስለዚህ እንደ ቡድን የዚህ አይነት የማሸነፍ ስሜት ሁላችንም ጋር እንደነበር ይሰማኛል።” ሲል ምላሹን ሰጥቷል።

Advertisements