ባየር ሙኒክ ከ ሪያል ማድሪድ | የሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

ሪያል ማድሪድ በተከታታይ ለሶስተኛ ዓመት ሻምፒዮን የመሆን ዕቅዱን ለማሳካት የቡንደስሊጋውን ኃያል ክለብ ባየር ሙኒክን ረቡዕ ምሽት በግማሽ ፍፃሜው በአሌያንዝ አሬና ይገጥማል።

የዚነዲን ዚዳኑ ቡድን በሩብ ፃሜው በጁቬንቱስ በመጨረሻ ሰዓት በተዓምር ከመሸነፍ መትረፍ የቻለ ሲሆን፣ በአንፃሩ ባየር ሙኒክ ሲቪያን በቀላሉ በማሸነፍ እዚህ ዙር ላይ መድረስ ችሏል።

ባየር ሙኒኮች በዚህ የውድድር ዘመን በሁሉም የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ በድምሩ 15 ግቦችን ማስቆጠር በቻለው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ ይህን ጨዋታ የሚያደርጉ ቢሆንም፣ ነገር ግን የየፕ ሄንክሱ የአጥቂ ክፍልም የሪያልን የተከላካይ ክፍል ሰብሮ የመግባት ከፍ ያለ በራስ መተማመን አለው።

ጨዋታው መቼ ይደረጋል?


ባየር ሪያል ማድሪድን በሙኒኩ አሊያንዝ አሬና የሚያስተናግድበት ጨዋታ ዛሬ (ረቡዕ) ሚያዝያ 17፣ 2010 ዓ.ም ምሽት 3:45 ላይ ይደረጋል።

ጨዋታውን እንዴት በቀጥታ መመልከት ይቻላል?


ይህ ጨዋታ በዩናይትድ ኪንግደም በቢቲ ስፖርት 2 የቴሌቪዥን ጣቢያና በቢቲ የኢንተርኔት ቀጥታ ስርጭት ሲተላለፍ፣ በአፍሪካ ከሰሃራ በታች ሱፐርስፖርት 3 እና በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ ቤንስፖርት 11 የቴሌቪዝን ጣቢያዎች ላይ በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል።

የቡድን ዜናዎች ምን ይመስላሉ?


ለባየር ትልቁ ዜና አርትሮ ቪዳል ገጥሞት ከነበረው የጉልበት ጉዳት አገግሞ ወደልምምድ የመመለሱ ጉዳይ ነው።

ነገር ግን የጀርመኑ ሻምፒዮን በጉዳት ምክኒያት ኪንግስሌይ ኮማንን እና ኮከቡን ግብ ጠባቂውን ማኑኤል ኑየርን በዚህ ጨዋታ ላይ እያገኝም።

የአምናው ሻምፒዮን ማድሪድ ብቸኛ ጉዳት ያለበት ተጫዋቹ ናቾ ብቻ ነው።

ሁለቱም ክለቦች ቅጣት ያለባቸው ምንም አይነት ተጫዋቾዥ የሏቸውም፡

ምን ዓይነት ግምታዊ አሰላለፎች ሊኖሩ ይችላሉ?


ባየር (4-2-3-1): ዩልሪች፣ ኪሚች፣ ቦአቲንግ፣ ሁመልስ፣ አላባ፣ ማርቲኔዝ፣ ቲያጎ፣ ሮበን፣ ሙለር፣ ኻመስ ሮድሪጌዝ፣ ሊቫንዶውስኪ

ሪያል ማድሪድ (4-3-3): ናቫስ፣ ካርቫኻል፣ ቫራን፣ ራሞስ፣ ማርሴሎ፣ ሞድሪች፣ ካስሚሮ፣ ክሩዝ፣ ኢስኮ፣ ቤንዜማ፣ ሮናልዶ

የሁለቱ ክለቦች እውነታዎች ምን ይመስላሉ?


  • ባየር ሙኒክ እና ሪያል ማድሪድ በአውሮፓውያኑ ዋንጫ/ሻምፒዮንስ ሊግ ሲገናኙ ይህ ለ25ኛ ጊዜ ሲሆን፣ በውድድሩ ላይ ብዙ ጊዜ በመገናኘትም የውድድሩን ክብረወሰን ይዘዋል። ሁለቱም እያንዳንዳቸው ለ11 ጊዜያት አሸንፈዋል።
  • ከ2011-12 የውድድር ዘመን ወዲህም ሁለቱ ክለቦች በግማሽ ፍፃሜው እርስበእርስ ሲገናኙ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ በ2011-12 የጀርመኑ ክለብ ወደቀጣዩ ዙር ሲያልፍ፣ በ2013-14 ደግሞ የስፔኑ ክለብ ወደቀጣዩ ክለብ አልፏል።
  • ባየር ሙኒክ በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመጨረሻ ጊዜ ከሪያል ማድሪድ ጋር ያደረጋቸውን አምስት ጨዋታዎች የተሸነፍ ሲሆን፣ ሁሉም ሽንፈቶች የገጠሙት ደግሞ በጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ላይ ነበር። (ሶስቱ በግማሽ ፍፃሜ እና ሁለቱ በሩብ ፍፃሜ)
  • ባየሮች በሎስ ብላንኮዎቹ በተከታታይ የደረሱባቸው አምስት ሽንፈቶች በውድድሩ ታሪክ በአንድ ክለብ የደረሰባቸው ከፍተኛው ሽንፈት ነው።
  • የፕ ሄንክስ በሻምፒዮንስ ሊጉ በሜዳቸው አሌያንዝ አሬና ካደረጓቸው 16 ጨዋታዎች 14ቱን በድል አጠናቀዋል። በእነዚህም 48 ግቦችን ሲያስቆጥር 10 ግቦች ብቻ ደግሞ ተቆጥሮበታል።
  • በሻምፒዮንስ ሊጉ በትንሹ 20 ጨዋታዎችን መምራት ከቻሉ አሰልጣኞች ይህ ጨዋታ ብዙ ጨዋታዎችን በማሸነፍ ከፍተኛ ልኬት ካላቸው የበላይ ሶስት አሰልጠኞቹ ሁለቱን ያገናኛል። (የየፕ ሄንክስ (71%) እና ዚዳን ዚዳን (67%)። ልዊስ ኢነሪኬ ብቻ ከሁለቱ አሰልጠኞች የላቀ (73%) በመቶ የማሸነፍ ልኬት አላቸው)
  • ክርስቲያኖ ሮናልዶ ባዳረጋቸው ባለፉት 11 የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ በእያንዳንዱ ላይ ቢያንስ አንድ ግብ ማስቆጠር ችሏል (በድምሩ 17 ግቦች)። ይህ ደግሞ በውድድሩ ታሪክ በተከታታይ ብዙ ጊዜ በመቆጠር ከፍተኛው ነው።
  • የ33 ዓመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሻምፒዮንስ ሊጉ በባየር ሙኒክ ላይ ዘጠኝ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። በውድድሩ በእንድ ክለብ ላይ ብዙ ግብ የማስቆጠር ክብረወሰን ያለው ብቸኛው ተጫዋችም
  • ራሱ ሮናልዶ ነው። (በጁቬንቱስ ላይ 10 ግቦችን አስቆጥሯል)
  • ይህ ጨዋታ በሻምፒዮንስ ሊጉ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ታሪክ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋቾችን ያገናኛል። (በዚህ ደረጃ ክርስቲያኖ ሮናልዶ 13 ግብ ሲያስቆጥር ሮበርት ሊቫንዶውስኪ ደግሞ ስድስት ግቦችን አስቆጥሯል።)
Advertisements