ቬንገር አርሰናል በራሳቸው ፍላጎት የመልቀቅ ውሳኔ ላይ እንዳለደረሱ ገለፁ

አርሰን ቬንገር በመጪው ክረምት ክለቡን በራሳቸው ውሳኔ ሳይሆን በግፊት እንዲለቁ መደረጋቸውን ገልፀዋል።

የ68 ዓመቱ አሰልጣኝ በመድፈኞቹ የነበራቸውን 22 ዓመታት የዘለቀ የአሰልጠኝነት ሚና ይህ የውድድር ዘመን ሲጠናቀቅ እንደሚለቁ ክለቡ በድረገፁ በይፋ የገለፀው ያለፈው አርብ ዕለት ነበር።

በመግለጫው ማግስት የክለቡ ዋና ስራአስፈፃሚ የሆኑት ኢቫን ጋዚደስ ከውሳኔው ሂደት ጀርባ ስላለው ነገር ከጋዜጠኞች ለቀረበላችው ጥያቄ “ውይይት ነበር። አርሰን ውሳኔ ላይ ደርሷል። ሂደቱ [ምትካቸውን የማፈላለጉ] አሁን ተጀምሯል።” ሲሉ ምለሽ ሰጥተው ነበር።

ይሁን እንጂ ቬንገር ሁልጊዜም በክለቡ ለፈረሙት ኮንትራት ታማኘኝ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ሲገለፁ ቆይተዋል። እናም ከክለቡ ጋር እስከ2019 ድረስ የሚዘልቅ ስምምነት እያላቸው ለምን አሁን ለመልቀቅ እንደፈለጉ ከጋዜጠኞች ለቀረበለቸው ጥያቄ ፈረንሳያዊው አሰልጣኝ “ጊዜው [ክለቡን የመልቀቂያው] በእርግጥም የእኔ ውሳኔ አይደለም። የተቀረውን ግን አስቀድሜም የተናገርኩት ነገር ነው።” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

ቬንገር ክለቡን የሚለቁባት ምክኒያት በማሰልጠን ስራቸው ላይ የደጋፊው ትዕግስት ማጣት እንደሆነ እሁድ ዕለት ገለፅው እንደነበር ይታወሳል።

Advertisements