የእግርኳሱ ዓለም ከፍተኛ ተከፋይ ተጫዋቾች እነማን ናቸው?

በምትሃተኛ እግሮቻቸው የዓለም እግርኳስ አድናቂውን ቀልብ መማረክ ከቻሉ የዓለማችን ከዋክብት መካከል የትኞቹ ተጫዋቾች ከፍተኛ ክፍያ እንደሚያገኙ አስበው ያውቃሉ?

ሊዮኔል ሜሲ አስገራሚ በሆነ 126 ሚሊዮን ዩሮ ዓመታዊ የክፍያ ዋጋ በዓለም አቀፉ እግርኳስ ላይ ከፍተኛ ተከፋይ ተጫዋች ነው!

ጥቅማ ጥቅሞችን እና የተለያዩ የማስታወቂያ ገቢዎችን ባካተተው በዚህ ዓመታዊ የክፍያ መጠንም አርጄንቲናዊው የባርሴሎና ኮከብ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ኔይማር እና ጋርዝ ቤል በብዙ መጠን በልጦ በቀዳሚነት መቀመጥ ችሏል።

ፍራንስ ፉትቦል በቅርቡ ባወጣው የዓለማችን ከፍተኛ ተከፋይ እግርኳስ ተጫዋቾች ዝርዝር መሰረትም 20 ከፍተኛ ተከፋይ ተጫዋቾች እና የሚያገኙት የክፍያ መጠን ከታች ያለውን ይመስላል።


#20 ማኑኤል ኑየር | ባየር ሙኒክ | ዋጋ: 20.8 ሚ.ዩሮ


#19 ፖል ፖግባ | ማንችስተር ዩናይትድ | 22 ሚ.ዩሮ


#18 ሮበርት ሊቫንዶውስኪ | ባየር ሙኒክ | 22.2 ሚ.ዩሮ


#17 ኦስካር | ሻንጋይ ሲአይፒጄ | 22.2 ሚ.ዩሮ


#16 ኤዲሰን ካቫኒ | ፒኤስጂ | 22.5 ሚ.ዩሮ


#15 ቶማስ ሙለር | ባየር ሙኒክ | 23 ሚ.ዩሮ


#14 ካሪም ቤንዜማ | ሪያል ማድሪድ | 23.5 ሚ.ዩሮ


#13 አሌክሲስ ሳንቼዝ | ማንችስተር ዩናይትድ | 23.55 ሚ.ዩሮ


#12 ኢዜኩዌል ላቬዚ | ሄቤ ቻይና ፎርቹን | 25.3 ሚ.ዩሮ


#11 አንድሬስ ኢንየስታ | ባርሴሎና | 25.5 ሚ.ዩሮ


#10 ልዊስ ስዋሬዝ | ባርሴሎና | 26 ሚ.ዩሮ


#9 አንቱዋን ግሪዝማን | አትሌቲኮ ማድሪድ | 26 ሚ.ዩሮ


#8 ዝላታን ኢብራሂሞቪች | ኤልኤ ጋላክሲ | 26.8 ሚ.ዩሮ


#7 ሰርጂዮ ራሞስ | ሪያል ማድሪድ | 27.5 ሚ.ዩሮ


#6 ቶኒ ክሩዝ | ሪያል ማድሪድ | 28.2 ሚ.ዩሮ


#5 ጄራርድ ፒኬ | ባርሴሎና | 29 ሚ.ዩሮ


#4 ጋርዝ ቤል | ሪያል ማድሪድ | 44 ሚ.ዩሮ


#3 ኔይማር | ፒኤስጂ | 81.5 ሚ.ዩሮ


#2 ክርስቲያኖ ሮናልዶ | ሪያል ማድሪድ | 94 ሚ.ዩሮ


#1 ሊዮኔል መሲ | ባርሴሎና | 126 ሚ.ዩሮ

Advertisements