ፍራንስ ፉትቦል አንድሬስ ኢኒየስታን ይቅርታ ጠየቀ

የፈረንሳዩ መፅሄት ፍራንስ ፉትቦል እስፔናዊው የባርሴሎና የኳስ ጥበበኛ አንድሬስ ኢንየስታን ይቅርታ ጠይቋል።

ላለፉት 15 አመታት ከባርሴሎና ጋር በድል የተሽቆጠቆጠ ጊዚያት ያሳለፈው አንድሬስ ኢኒየስታ ከካታላኑ ቡድን ጋር ለመለያየት ተቃርቧል።

በእድሜው መግፋት ምክንያት ቡድኑን እንደ ቀደሙት አመታት ሁልጊዜ ማገልገል ባለመቻሉ ወደ ቻይና እንደሚያቀና ይጠበቃል።

ስፔናዊ ጥበበኛ ባለፈው ሳምንት በስፔን የንጉስ ዋንጫ ሲቪያን ሲያሸንፉ ድንቅ ብቃት በማሳየት ቡድኑ የዋንጫ አሸናፊ ማድረግ ችሏል።

የስፔን ላሊጋ ዋንጫም አሸናፊው ባርሴሎና በይፋ አሸናፊነቱን ለማወጅ ቀናት ብቻ የሚቀሩት ሲሆን ይህም ለስፔናዊው ተጫዋች በህይወቱ ያገኛቸው የዋንጫን ቁጥር ከፍ የሚያደርግለት ይሆናል።

በብዙዎቹ የእግርኳስ ወዳጆች ቀለል አድርጎ በሚያደርገው እንቅስቃሴ የሚወደደው ኢንየስታ ለ ሀገሩ ስፔንም የአለም ዋንጫ እንድታገኝ ያደረገው አስተዋፅኦ አይረሳም።

በተለይም በ 2010 የአለም ዋንጫ ላይ በፍፃሜ ጨዋታ ላይ ያስቆጠራት ጎል ስፔን የአለም ዋንጫውን ከፍ እንድታደርግ ማድረጉ ይታወሳል።

የፈረንሳዩ መፅሄት ፍራንስ ፉትቦል ይህ ጥበበኛ ስፔናዊ ላለፉት ረጅም አመታት ያሳለፈው ድንቅ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማት ባለመሸለሙ ይቅርታ ጠይቆታል።

መፅሄቱ በተለይ 2010 ላይ የነበረው የባሎንዶር ሽልማት ኢንየስታ ባለመሸለሙ መፀፀቱን አሳውቋል።

Advertisements