አርሰናል ከ አትሌቲኮ ማድሪድ | የዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍፅሜ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

አርሰናል አሰልጣኙ አርሰን ቬንገር ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ጋር የመጨረሻቸውን የአውሮፓውያኑ ውድድር ዋንጫን በማንሳት እንዲሰናበቱ ተስፋ በማድረግ በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድን ይገጥማል።


ቬንገር ምንም እንኳ አሁን ከክለቡ ጋር ያላቸው ኮንትራት አንድ ቀሪ ዓመት ቢቀረውም ባለፈው አርብ ግን በውድድር ዘመኑ መጨረሻ አርሰናልን እንደሚለቁ በመግለፅ የእግርኳሱን ዓለም ድንጋጤ ውስጥ ከተው ነበር።

ይህ ዜናም ማድፈኞቹ ለአልጣኙ ማልካም ስንብት ይሆናቸው ዘንድ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ በጥንካሬ እንዲጫወቱ ሊያደረጋቸው እንደሚችል ቢጠበቅም፣ ነገር ግን የዲያጎ ሲሞኒው ቡድን ባለፉት አራት የውድድር ዘመናት በፍፃሜው በቀንደኛው የከተማው ተቀናቃኙ ሪያል ማድሪድ ሁለት ጊዜ ያህል የተሸነፉበትን ጨዋታ በቀላሉ ባለመዘንጋት የቬንገርን የደስታ ስንብት መልካም ላያደርጉት ይችላሉ።

ጨዋታው መቼ ይደረጋል?


አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን በኤመራትስ ስታዲየም የሚያስተናግድበት ይህ የለንደን ከተማ ጨዋታ ዛሬ (ሀሙስ) ምሽት 4፡05 ላይ የሚደረግ ነው።

ጨዋታውን እንዴት በቀጥታ መመልከት ይቻላል?


ይህ ጨዋታ ከሰሃራ በታች በአፍሪካ በሱፐር ስፖርት 3 የቴሌቪዥን ቻናል፣ በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ደግሞ በቤን ስፖርት 11 እንዲሁም በዩናይትድ ኪንግደም በቢቲ ስፖርት 2 እና ቢቲ ስፖርት 4ኬ ቻናሎች ላይ በቀጥታ ይተላለፋል።

የክለቦቹ የከዚህ ቀደም የእርስ በርስ ግንኙነት ምን ይመስላል?


አርሰናል እና አትሌቲኮ ማድሪድ በአውሮፓ መድረክ የነጥብ ጨዋታዎዥ ላይ ፈፅሞ ተገናኝተው አያውቁም። ነገር ግን መድፈኞቹ እ.ኤ.አ. በ2009 በቅድመ ውድድር ዘመን በኤመራትስ ዋንጫ አትሌቲኮን 2ለ1 ማሸነፍ ችለዋል።

ስለቡድኖቹ ምን አይነት ዜናዎች አሉ?


አርሰናል በሃሙሱ ጨዋታ የጃክ ዊልሼር፣ ፐር ሜርትሳከር እና መሱት ኦዚልን ግልጋሎት መልሶ ያገኛል።

የቁርጭምጭሚት ጉዳት የነበረበት ዊልሼር፣የዳሌ ጉዳት የነበረበት ቼክ እና ህመም ላይ የነበረው ኦዚም ዌስትሃምን ባሸነፈው የአርሰናል ቡድን ውስጥ ተካተው አልተጫወቱም። ሌላ የቁርጭምጭሚት ጉዳት ሰለባ ሆኖ የቆየው ሲያድ ኮላሲናችም ለዚህ ጨዋታ ዝግጁ የሆነ ሌላኛው ተጫዋች ነው።

የጉልበት ገዳት ያለበት ሄነሪክ ሚክሂታሪያን፣ የቁርጭምጭሚት ጉዳት ያለበት ሞሐመድ ኤልኒኒ እና የቆየ የተረከዝ ጉዳት ያለበት ሳንቲ ካዛሮላ አሁንም ከሜዳ እንደራቁ የሚቆዩ ሲሆን፣ ፒየር-ኤመሪክ አውባምያንግ ደግሞ በጨዋታ ተገቢነት በዚህ ጨዋታ ላይ መስለፍ የማይችል ሌላኛው ተጫዋች ነው።

በአንፃሩ የአትሌቲኮው አሰልጠኝ ሲሞኒ ዲያጎ ኮስታ ከመልካም አቋም ላይ እንደሚገኝና የአርሰናልን የተከላካይ ክፍል ዳግመኛ የማሸበሩን ስራ እንደሚመራ ገልፀዋል።

ምን አይነት የመጀመሪያ አሰላለፎች ይጠበቃሉ?


አርሰናል (4-3-3): ቼክ፣ ቤለሪን፣ ሙስታፊ፣ ኮሺይልኒ፣ ሞንሪል፣ ዣካ፣ ዊልሼር፣ ራምሲ፣ ኦዚል፣ ዌልቤክ፣ ላካዜቴ

አትሌቲኮ (4-4-2): ኦብላክ፣ ቭርሳሊኺኮ፣ ጎዲን፣ ሳቪች፣ ኸርናንዴዝ፣ ኮኬ፣ ጋቢ፣ ሳኡል ኒጉዝ፣ ኮሪያ፣ ኮስታ፣ ግሪዝማን

Advertisements