ዝላታን ኢብራሂሞቪች በዓለም ዋንጫው ላይ አይጫወትም

ከዓለማቀፋዊ ውድድሮች ራሱን አግልሎ የሚገኘው ዝላታን ኢብራሂሞቪች በስዊድን ብሄራዊ ቡድን ተመለሶ በዓለም ዋንጫው ላይ እንደማይጫወት የስዊድን እግርኳስ ማህበር ገልፅዋል።

የ36 ዓመቱ አጥቂ በስዊዲን ብሄራዊ ቡድን ውስጥ የነበረውን የጨዋታ ዘመን የቋጨው በ2016ቱ የአውሮፓ ዋንጫ ላይ የነበረ ቢሆንም፣ ነገር ግን ብዙዎችን ባስገረመ ሁኔታ የፊታችን ሰኔ ወር ላይ በሚደረገው የዓለም ዋንጫ ብሄራዊ ቡድኑን ተቀላቅሎ እንደሚጫወት አስተያየቶች ሲሰጡበት ቆይቷል።

አሁን በአሜሪካኑ ክለብ ኤልኤ ጋላክሲ እየተጫወተ የሚገኘው ኢብራሂሞቪች በውድድሩ ላይ ፍፁም በቀድሞ አቋሙ ላይ ሊገኝ እንደሚችልም ተናግሯል።

ይሁን እንጂ ተጫዋቹ አሁን በጄን አንደርሰን በሚመራው የስዊዲን ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ተካቶ አይጫወትም።

የስዊዲን እግርኳስ ማህበር በፌስቡክ ገፁ ላይ ባወጠው መግለጫ “የብሄራዊ ቡድኑ የምንጊዜውም የስዊዲን ታላቅ ግብ አስቆጣሪው
በዓለም ዋንጫው ላይ አይጫወትም።” ሲል ገልፅዋል።

የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጠኝ አንደርሰን ባለፈው ምት ስለኢብራሂሞቪች መመለስ እንዳልተናገሩ ገልፀው፣ ነገር ግን በውድድሩ ላይ የመጫወት ውሳኔው የተጫዋቹ እንደሆነ ገልፀው ነበር።

“[ኢብራሂሞቪች] መጫወት እንደሚፈልግ እስካሁን አላናገረኝም። ” በማለት አንደርሰን ለጀርመኑ ጋዜጣ ቢልድ ተናግረው፣ አክለውም “ውሳኔ ላይ የሚደርስ ከሆነ ከዩሮ 2016 በኋላ መጫወት እንዳቆሙት [ተጫዋቾች] ሁሉ ስለዚያ ደውሎ ሊያናግረኝ ይችላል። ” ሲሉ ገልፀዋል።

Advertisements